የአልሸባብ ጥቃት እየተጠናከረ መምጣት | ኢትዮጵያ | DW | 25.08.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአልሸባብ ጥቃት እየተጠናከረ መምጣት

አልሸባብ ሞቃዲሾን እያመሳት ነው። ትላንት የፈጸመው ጥቃት ለዚያች ሀገር እየተደረገ ያለውን ዓለም አቀፍ ጥረት መና እንዳያስቀረው በእርግጥ እየተሰጋ ነው።

default

ሞቃዲሾ

በትናትናው ዕለት ሞቃዲሾ በሚገኘው የሽግግሩ መንግስት ቤተመንግስት አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ሆቴል በአልሸባብ በተቀነባበረ የቦምብ ጥቃት6 የምክርቤት አባላትን ጨምሮ 32 ሰዎች ሲገደሉ በዛሬው ዕለትም ውጊያው እንደቀጠለ ከስፍራው ከሚወጡ ዘገባዎች ለመረዳት ተችሏል። አንድ ጋዜጠኛ በዛሬው ውጊያ ከተገደሉት 6 ሰዎች ውስጥ እንደሚገኝበት ተነግሯል። የአልሸባብ የሰሞኑ ማየል ሶማሊያን ወደየት ይወስዳት ይሆን? ኢትዮዽያ ዳግም ወደሶማሊያ ሳትገባ አትቀርም የሚለው የፖለቲካው ተንታኞች ግምት አሁን ላይ በሰፊው እየተሰማ ነው። አርያም ተክሌ የአለም አቀፉን የግጭት ቡድን የሶማሊያ ተንታኝን ያነጋገረችበ ዘገባ ቀጥሎ ይቀርባል።

አርያም ተኬ
ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic