የአልሲሲ የፈረንሳይ ጉብኝት እና የመብት ተሟጋቾች ተቃውሞ  | ዓለም | DW | 25.10.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የአልሲሲ የፈረንሳይ ጉብኝት እና የመብት ተሟጋቾች ተቃውሞ 

የመብት ተሟጋች ተቋማት የአል ሲሲ መንግሥት ጋዜጠኞችን፣የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን እንዲሁም ግለሰቦችን ከማሰር ባለፈ ቁም ስቅል ይፈጽምባቸዋል ሲሉ ይወቅሳሉ። የፈረንሳይ መንግሥትም ከአልሲሲ ጋር ምንም ዓይነት ኤኮኖሚያዊም ሆነ ወታደራዊ ስምምነት እንዳያደርግም ጠይቀዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:53

የአል ሲሲ የፈረንሳይ ጉብኝት እና ተቃውሞው

ፈረንሳይን በመጎብኘት ላይ ያሉት የግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ አምነስቲ ኢንተርናሽናልንን እና ሂዩመን ራይትስ ዋች ከመሳሰሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። እነዚህ የመብት ተሟጋች ተቋማት የአል ሲሲ መንግሥት ጋዜጠኞችን፣የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን እንዲሁም ግለሰቦችን ከማሰር ባለፈ ቁም ስቅል ይፈጽምባቸዋል ሲሉ ይወቅሳሉ። የፈረንሳይ መንግሥትም ከአልሲሲ ጋር ምንም ዓይነት ኤኮኖሚያዊም ሆነ ወታደራዊ ስምምነት እንዳያደርግም ጠይቀዋል። የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኤማኑዌል ማክሮም ግብጽ ለራስዋ ስትል ሰብዓዊ መብቶችን እንድትጠብቅ ጠይቀዋል። አል ሲሲ ግን ከመብት ተሟጋቾች የሚቀርቡባቸውን ክሶች አስተባብለዋል። የፓሪስዋ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ ዝርዝሩን ልካልናለች። 
ሃይማኖት ጥሩነህ 
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic