የአሌ ልዩ ወረዳ ምክር ቤት የቀረበለትን አስተዳዳሪ ሹመት ውድቅ አደረገ | ኢትዮጵያ | DW | 22.10.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአሌ ልዩ ወረዳ ምክር ቤት የቀረበለትን አስተዳዳሪ ሹመት ውድቅ አደረገ

በደቡብ ክልል የአሌ ልዩ ወረዳ ምክር ቤት አስቸኳይ ገባኤ በገዢው ፓርቲ የቀረበለትን የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ሹመት በአብላጫ ድምፅ ውድቅ አደረገ ።  ምክር ቤቱ የዋና አስተዳዳሪውን ሹመት ሳይቀበለው የቀረው በእጩነት የቀረቡት ግለሰብ የማስፈጸም አቅም የላቸውም በሚል መሆኑን የልዩ ወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:11

ውድቅ የተደረገው የአሌ ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪ ሹመት

በደቡብ ክልል የአሌ ልዩ ወረዳ ምክር ቤት አስቸኳይ ገባኤ በገዢው ፓርቲ የቀረበለትን የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ሹመት በአብላጫ ድምፅ ውድቅ አደረገ ። 
ምክር ቤቱ የዋና አስተዳዳሪውን ሹመት ሳይቀበለው የቀረው በእጩነት የቀረቡት ግለሰብ የማስፈጸም አቅም የላቸውም በሚል መሆኑን የልዩ ወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገኒሶ ገሳቶ ለዶቼ ቬለ (DW) ገልጸዋል።  ዶቼ ቬለ (DW) ያነጋገራቸውና ሹመቱ ውድቅ የተደረገባቸው እጩ በበኩላቸው የምክር ቤቱን ውሳኔ የሚቀበሉት ቢሆንም በሂደቱ ግን አሻጥር ተሰርቶብኛል ይለሉ። 

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 
ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሐመድ
 

Audios and videos on the topic