የአለም የገንዘብ ቀዉስና ድሆቹ ሐገራት | ኢትዮጵያ | DW | 21.11.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአለም የገንዘብ ቀዉስና ድሆቹ ሐገራት

አክጁዝ እንደሚያምኑት ግን የገንዘብ ቀዉሱ እስያና ደቡብ አሜሪካን የሚጎዳዉን ያክል አፍሪቃን አይጎዳም።

default

የአፍሪቃ የግብርና ምርቶች

የድሆቹ ሐገራትን ችግር ማቃለል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚነጋገር አለም አቀፍ ጉባኤ በመጪዉ ሳምንት አርብ ዶሐ-ቀጠር ላይ ይደረጋል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በጠራዉ ጉባኤ ላይ የሐገራት መሪዎች፥የገንዘብ ሚንስትሮች፥ የገንዘብ ተቋማት ሐላፊዎችና የንግድ ድርጅት ተወካዮች ይካፈላሉ።የበለፀገዉ አለም ክፍተኛ የገንዘብ ቀዉስ በገጠመዉ ባሁኑ ወቅት የሚደረገዉ ጉባኤ የድሆቹን ሐገራት ችግር ለማቃለል ሁነኛ እርምጃ መዉሰዱ ግን ብዙ አጠራጣሪ ነዉ።አብዱላሒ ታኮ ቤላ ያዘጋጀዉን ነጋሽ መሐመድ አጠናቅሮታል።