የኖቤል የሰላምተሸላሚው የአውሮፓ ህብረት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 11.12.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የኖቤል የሰላምተሸላሚው የአውሮፓ ህብረት

ሶስት የኖቤል የሰላም ተሸላሚዎችም የአውሮፓ ህብረት የኖቤል ተሸላሚ መሆኑን ተቃውመዋል ። ከጥቂት ቀናት በፊት ለኖቤል ኮሚቴ በጋራ በፃፉት ደብዳቤ የህብረቱ ተግባራት ሽልማቱ የሚወክላቸውን እሴቶች ይቃረናል ሲሉ ተቃውሞአቸውን ገልፀዋል ።አንዳንድ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላትም በሽልማቱ አለመስማማታቸውን ተናግረዋል ።

የአውሮፓ ህብረት ትናንት ኦስሎ ኖርዌይ ውስጥ በተካሄደ ስነ ስርዓት የኖቤል የሰላም ሽልማት ተበርክቶለታል ። የአውሮፓ ህብረት ለዚህ ሽልማት መብቃት የአውሮፓ መንግሥታትን ስያስደስት ሽልማቱ ለህብረቱ አይገባም ሲሉ የሚከራከሩ ወገኖችን ደግሞ ቅር አሰኝቷል ።
« የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ የ 2012 የኖቤል የሰላም ሽልማት ለአውሮፓ ህብረት እንዲሰጥ ወስኗል ። ህብረቱና እዚህ ደረጃ ያደረሱት ቀደምት ማህበራት ከ60 አመታት በላይ ለሠላም ለእርቅና ለዲሞክራሲ መስፈን እንዲሁም ለሰብአዊ መብቶች አስተዋጽኦ አበርክተዋል ። »
የኖርዌይ የሰላም ኮሚቴ ሊቀመንበር ቶርብዮርን ያግላንድ እጎአ ጥቅምት 12 ፣ 2012 ኦስሎ ኖርዌይ ውስጥ የአውሮፓ ህብረት የ 2012 የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆኑን  ሲያሳውቁ ቅሬታቸውን በለሆሳስ የገለጹ ነበሩ ። ያግላንድ ንግግራቸውን በመቀጠል የኖቤል ኮሚቴ ውሳኔውን ያሳለፈበትን ምክንያት በዝርዝር አስረዱ ።  
«የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ እጅግ ጠቃሚ አድርጎ በሚያያቸው የአውሮፓ ህብረት ለሠላምና ለእርቅ እንዲሁም ለዲሞክራሲና ለሰብዓዊ መብቶች ባካሄዳቸው ስኬታማ ትግሎች የተገኙት ውጤቶች ላይ ማተኮር ይፈልጋል ። የአውሮፓ ህብረት መረጋጋትን ለማስፈን ባበረከተው ድርሻ አብዛኛውን አውሮፓን ከጦርነት ክፍለ ዓለም ወደ ሠላም ክፍለ ዓለም ቀይሯል ። » ምንም እንኳን የኖቤል የሠላም ኮሚቴ

በነዚህ ምክንያቶች የአውሮፓ ህብረትን ለኖቤል የሠላም ሽልማት መምረጡን ቢያሳውቅም ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹን አምነስቲ ኢንተርናሽናልና የአውሮፓ ህብረት የሥራ ባልደረቦችን ጭምር የመሳሰሉ በርካታ ተችዎች ህብረቱ ለሽልማቱ የተመረጠበት ምክንያት አላሳመናቸውም ። በነዚህ ወገኖች አስተያየት በየቀኑ በሜዲቴራንያን ባህር አድርገው በትናንሽ ጀልባዎች ከሰሜን አፍሪቃ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክሩ በርካታ ሰዎች መንገድ ላይ ህይወታቸው ማለፉን መስማትና ማየት የተለመደ ክስተት ሆኗል ። ከአረቡ ዓለም ህዝባዊ አብዮት ወዲህ ወደ አውሮፓ የሚጎርፈው ስደተኛ ቁጥር እጅግ እየጨመረ ነው ። ይህም አሁን አውሮፓን በእጅጉ እየተፈታተናት ነው ። ድንበሮች ክፍት መሆናቸውን በእጅጉ የሚያበረታታው የአውሮፓ ህብረት ፍልስፍና ወደ ህብረቱ አባል ሃገራት ለመግባት የሚፈልጉ ስደተኞችን በመከልከል እየተፈተነ ነው ። የህብረቱ አባል ሃገራት በተለይ ህብረቱ ህገ ወጥ በሚላቸው ስደተኞች ጉዳይ ላይ ለአመታት መግባባታ እንደተሳናቸው ነው ። ስደተኞቹ ከሃገራቸው ስለሚያባርሩባቸው ሁኔታዎች እንዲሁም ለሚመጡባቸው ሃገራት እርዳታ መስጠትን በተመለከተም አባላቱ የተለያየ አቋም ነው ያላቸው ። በዚህ የተነሳም አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ህብረቱ ሙሉ በሙሉ ሽልማቱ አይገባውም የሚሉት ። ከነዚህም አንዱ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የጀርመን ቅርንጫፍ ዋና ፀሃፊ ቮልፍጋንግ ግሬንትስ ናቸው ። ግሬንትስ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት ስደተኞች በሜዲቴራንያን ባህር ህይወታቸውን እንዲያጡ ሰበቡ የህብረቱ ፖሊሲ ነው ሲሉ ተናግረዋል ።
«በማዕከላዊው ባህር ፣ ሰዎች  ህይወታቸውን እስከማጣት የሚደርሱት በአውሮፓውያኑ ነጣይ  (የሚለይ ፤የሚያገል)ፖለቲካ ሳቢያ ነው።»

ቮልፍጋንግ ኬለር

EU Symbolbild Friedensnobelpreis Flagge Europäische Union


በግሬንትስ እምነት ይህ በአስቸኳይ መለወጥ አለበት ። ህብረቱም በዚህ ረገድ ሃላፊነቱን መወጣት ይገባዋል ። ግሪንትስ በተለይ በቱርክና በግሪክ ድንበር በኩል ያለውን ከፍተኛ የድንበር ቁጥጥርም ይቃወማሉ ። በርሳቸው አስተያየት በዚህ ምክንያት አመፅና ጥቃትን ሸሽተው ወደ አውሮፓ የሚሰደዱ በርካታ ሰዎች እጅግ አደገኛ በሆኑ መንገዶች ማለትም ለባህር ላይ ጉዞ ባልተሰሩ ጀልባዎች ጭምር እየተጫኑ በአደገኛው የሜዲቴራንያን ባህር ለመጓዝ እየተገደዱ ነው ። ከዚህ ሁሉ ስቃይ በኋላ ከሞት ተርፈው በባህር ላይ ሲያዙም ደግሞ ሌላ ፈተና ነው የሚጠብቃቸው ።   
«ሰዎች በማዕከላዊው ባህር ከተያዙ በኋላ ተገን ፈላጊነታቸውን ቢገልጹም እንኳ ይህ ዕድል አብዛኛውን ጊዜ ይነፈጋቸዋል። «ስደተኞች ነን» ካሉ ይኸው ጉዳያቸውም ሆነ ማመልከቻቸው በአንድ  የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገር መታየት ይኖርበታል። ግን ይህ አይደረግም።»
ወደ አውሮፓ ከሚሰደዱት አብዛኛዎቹ ከ 16 እስከ 30 አመት የሚሆናቸው ወጣቶች ናቸው ። የሚሰደዱትም ሥራ ፍለጋ ነው ። በዚህ የተነሳም ህብረቱ ጦርነት ሸሽተው የመጡ ተገን ጠያቂ ሳይሆን የኢኮኖሚ ስደተኛ ነው የሚላቸው ። በዚህ ምክንያትም ነው በአውሮፓ ህብረት ህግ መሰረት ወደ መጡበት እንዲመለሱ የሚደረገው ።
ግሬንዝ ከዚህ ሌላ አባል ሃገራት አፅድቀው ብሔራዊ ህጋቸው ውስጥ ያካተቱት የህብረቱ ፀረ አድልዎ መመሪያዎች በትክክል አለተገበሩም ይላሉ ለዚህም በምሳሌነት የሚጠቅሱት ጂፕሲ ወይም ሮማ ተብለው በሚጠሩት አናሳ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚደርሰውን አድልዎ ነው ።  

Berlin/ Der Generalsekretaer der Nichtregierungsorganisation (NGO) Amnesty International Deutschland, Wolfgang Grenz, gestikuliert am Mittwoch (23.05.12) in Berlin waehrend der Vorstellung des Reports 2012 Zur weltweiten Lage der Menschenrechte. Der Report liefert eine Bestandsaufnahme zur Ausgestaltung der Menschenrechte in 155 Laendern und Territorien. (zu dapd-Text) Foto: Andreas Prost/dapd

ቮልፍጋንግ ኬለር


«የትምህርት ፤ የህክምና አገልግሎት፤ የመኖሪያ ቤትና የሥራ ዕድል እንደ ሌሎች ዜጎች፤ እኩል አይደለም የሚያገኙት---።   ከዚህ በተጨማሪ  በአንዳንድ  አባል አገሮች፣ ለምሳሌ ያህል በጂፕሲዎች(ሲንቲ -ሮማ ) ላይ የኅይል እርምጃ ሲወሰድባቸው ፤ ዐይተው እንዳላዩ በቸልታ ነው የሚያልፉት። ይህ በአርግጥ አነጋጋሪ ነጥብ ነው። የአውሮፓው ኅብረት ወደፊት በዚህ ጉዳይ ላይ ጥብቅ እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል።»
ይህም እጅግ አነጋጋሪ ጉዳይና የህብረቱ አባል ሃገራት የሚጠበቅባቸውን እያደረጉ አለመሆናቸውን አመልካች ነው ይላሉ ግሬንትስ ። በዚህ ረገድም ህብረቱ ወደፊት ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል ። ይህን መሰሉን ትችት የሚሰነዝሩት ግሬንትስ ብቻ አይደሉም ።ሶስት የኖቤል የሰላም ተሸላሚዎችም የአውሮፓ ህብረት የኖቤል ተሸላሚ መሆኑን ተቃውመዋል ። እነርሱም የደቡብ አፍሪቃው ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱ ፣ የሰሜን አየርላንድ የሠላም ተሟጋች ሜይሪድ ማግዊሬ እንዲሁም አርጀንቲናዊው የሲቪል መብት ተሟጋች አዶልፎ እስክዊቭል ከጥቂት ቀናት በፊት ለኖቤል ኮሚቴ በጋራ በፃፉት ደብዳቤ የህብረቱ ተግባራት ሽልማቱ የሚወክላቸውን እሴቶች ይቃረናል ሲሉ ተቃውሞአቸውን ገልፀዋል ።አንዳንድ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላትም በሽልማቱ አለመስማማታቸውን ተናግረዋል ። በምክር ቤቱ የአረንጓዴ ፓርቲ ተወካይ ፍራንቼስካ ኬለር ህብረቱ ለሠላም ያደረገውን አስተዋጽኦ አስታውሰው ሆኖም አሁን በተቃራኒው የሚከናወኑ ተግባራት እየተፈፀሙ መሆኑን ሳያወሱ አላለፉም ።  
«እንዲያው በአሁኑ ቅጽበት የምናየው፣ የሚነገርለትን ተቃራኒ ነው። በውጭ አመራር፤ በንግድና በግብርና ው ፖለቲካ ወይም ደግሞ ስደተኞችን በሚመለከተው ፖለቲካችን፣ በሌላ አካባቢ ሰዎች ሥቃይ እንዲያዩ አስተዋጽኦ ማድረጉን እንገነዘባለን።»

Pressefotos http://www.ska-keller.de

ፍራንቼስካ ኬለር


ለአየር ንብረት ለውጥም ህብረቱ በመጠኑም ቢሆን ተጠያቂ መሆኑን ኬለር አልሸሸጉም ። እንደርሳቸው ህብረቱ ሙሉ በሙሉ ሊወደስም ሆነ ራሱን ሊያወድስ አይችልም ። በሌላም በኩል ህብረቱ ለሰላም ያደረገው አስተዋፅኦ የማይካድ ነው ። 2 የአለም ጦርነቶች ያሳለፈችው አውሮፓ የሰላም ዋስትና መሆኗ ግልፅ ነው ። ከበርሊን ግንብ መፍረስ በኋላ የማዕከላዊና የምሥራቅ አውሮፓ ሃገራት መቀራረብ በታሪካዊ ድልነት ተመዝግቧል ። ይህም በየሃገራቱ የሰብአዊ መብት ይዞታ መሻሻልን አስከትሏል ። አሁን ደግሞ ትኩረቱ ሁሉ ወደ ዩሮ ቀውስ ሆኖ የሰብአዊ መብትና የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ወደ ጎን እየተገፉ ነው ይላሉ ኬለር  
,«ይህን እንደ ማስጠንቀቂያ ምልክት ፣ እንደማስጠንቀቂያ ተኩስ ነው የአውሮፓው ኅብረት ሊመለከተው የሚገባ! አሁን በመጨረሻ፤ ለተጠቀሱት ሰብአዊ መብቶች፤ ለነጻነት መብትና  ለሰላም እንዲሁም ለመሳሰሉት ጥብቅና መቆም ይጠበቅበታል። አሁን ባለው ሁኔታ እጅግ የተጓደለ ነውና!»

 በዚያም  ሆነ በዚህ ፣ የአውሮፓው ኅብረት ፤ ዝናው፤ ስሙ እንዲጎድፍ  ስለማይፈለግ፣ ስለዚህ ጉዳይ መናገር አይቻልም። »

ትናንት ኦስሎ ኖርዌይ ውስጥ በተካሄደው በኖቤል የሰላም ሽልማት አሰጣጥ ስነ ስርዓት ላይ የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የጀርመን የፈረንሳይና የኔዘርላንድስን ጨምሮ 20 የአውሮፓ መንግሥታት መሪዎች ተገኝተዋል ።

Audios and videos on the topic

 • ቀን 11.12.2012
 • ቁልፍ ቃላት EU
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/1706h
 • ቀን 11.12.2012
 • ቁልፍ ቃላት EU
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/1706h