የኖቤል ተሸላሚዎችና የወጣት ተመራማሪዎች ጉባዔ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 02.07.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የኖቤል ተሸላሚዎችና የወጣት ተመራማሪዎች ጉባዔ

በያመቱ በሰሜኑ ንፍቀ ክበብ ሞቃት ወራት ፣ በሳይንስ የኖቤል ሽልማት ያገኙ ጠበብት ከታዳጊ ሳይንቲስቶች ጋር ተገናኝተው ሐሳብ የሚለዋወጡበት ጉባዔ ዘንድሮም ፣ ባለፈው እሁድ በደቡባዊቷ የቦደን ሴ (ቦደን ባህር ) ጠረፍ ከተማ ተጀምሮ እስከፊታችን

ዓርብ በመካሄድ ላይ ነው። በዚህ በ 64ኛው ጉባዔ ፤ 37 የኖቤል ሽልማት ያገኙ ጠበብትና 600 ያህል ወጣትና ጎልማሣ የሳይንስ ተመራማሪዎች ናቸው ተገናኝተው በመወያየት ላይ ያሉት። ጉባዔተኞቹ፣ የበጎ ምኞት መግለጫ መልእክት ከምድር ብቻ ሳይሆን ከሕዋም ደርሷቸዋል። ባለፈው ግንቦት ወደ ዓለም አቀፉ የሕዋ ምርምር ጣቢያ የተጓዙት ጀርመናዊው ተመራማሪና ጠፈርተኛ አሌክሳንደር ጌርስት ፣ ጉባዔው በተከፈተ ዕለት ፣ በቪዲዮ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን፤

«እያንዳንዳችሁ ፣ በሳይንሱ ዓለም፤ የ 21ኛው ምዕተ-ዓመት ኮሎምበስ ናችሁ» ማለታቸው ተጠቅሷል ። በ ሺ የሚቆጠሩ ገና የዶክተርነት ማዕረግ ለማግኘት በትምህርት ላይ የሚገኙ፣ እንዲሁም ማዕረጉን ካገኙ በኋላም በቀጣይነት ምርምር የሚያካሂዱ ፤ በጠቅላላ ከ 80 ያህል ሃገራት የተሰባሰቡ የኖቤል ተሸላሚዎችና ወጣት ተመራማሪዎች ናቸው በመሳተፍ ላይ ያሉት። በዘንድሮው ጉባዔ የተከሠተ አዲስ ነገር ቢኖር ዕድሜአቸው ከ 35 ዓመታ በታች ከሆነው ወጣት ተማራማሪዎች መካከል፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በቁጥር ላቅ ብለው የተገኙት ሴቶች ተመራማሪዎች መሆናቸው ነው።

አምና ላቅ ያለ ትኩረት የተደረገበት ርእሰ ጉዳይ ሥነ ቅመማ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ ለጤንነት እጅግ ጠንቀኛ የሆኑ በሽታዎችን በመከላከል ረገድ ላይ ነው ያተኮረው። ይህም፤ የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም በማጠናከርና ካንሠርን መቋቋም የሚያስችሉ ፍቱን መድኃኒቶችን ለማግኘት መጣርን ነው የሚመለከተው።

የጀርመን የትምህርትና የምርምር ሚንስትር ዶ/ር ዮሐና ቫንካ መርቀው በከፈቱት ጉባዔ በመሳተፍ ላይ ከሚገኙት መካከል ከዩናይትድ ስቴትስ የህክምና ተመራማሪ ራንዲ ሼክና ያምናው በሥነ ቅመማ የኖቤል ተሸላሚ እሥራኤላዊ አሜሪካዊው አሪዬ ቫርሸል ተጠቅሰዋል።

እ ጎ አ ከ 1901 ዓ ም አንስቶበያመቱ ፣ በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቀውን የኖቤል ሽልማት ለማግኘት የማይመኝ የሳይንስ ተማራማሪ ይኖራል ብሎ መገመት ያስቸግር ይሆናል። ተሳክቶላቸው በየጊዜው ከፍኛውን ሽልማት የሚያገኙትና በሙያው አንቱ የሚሰኙት ሊቃውንት፥ ተመራማሪዎች፣ የኖቤል ሽልማት የማግኘት ዕድል ከገጠማቸውና ፣ የተሣካላቸው ፣ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጠበት ዓመት በኋላ ምንድን ነው የሚያደርጉት? በምርምር ዓለም አቀፍ ጠቀሜታ ያለው ተግባር በኅብረትም ሆነ በተናጠል እስከምን ድረስ ነው የሚያከናውኑት?

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic