የኖርማንዲ ዘመቻ 75ኛ ዓመት መታሰቢያ | ራድዮ | DW | 06.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ራድዮ

የኖርማንዲ ዘመቻ 75ኛ ዓመት መታሰቢያ

የተባባሪዎቹ ሐገራት ወታደሮች፣ ከአዉሮፕላን እየወረዱ ፈረንሳይን ይቆጣጠሩ ከነበሩ የጀርመን ጠላቶቻቸዉ ጋር የገጠሙት ዉጊያ ብዙ ሺሕ  ሠራዊት ያለቀበት፣ የቆሰለና የተማረከበት ግን የጦርነቱን የኃይል ሚዛን የቀየረ ዉጊያ ነበር።

በሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወቅት የናትሴ ጀርመንን ለመዉጋት ያበሩት ሐገራት ጦር ኖርማንዲ ባሕር ዳርቻ፣ ፈረንሳይ ያረፈበት 75ኛ ዓመት ተከብሮ ዋለ።በበዓሉ ላይ በጦርነቱ የተሳተፉ ሐገራት መሪዎች፣ በሕይወት የሚኖሩ የቀድሞ ወታደሮችና የተለያዩ ሐገራት መልዕክተኞች ተካፋዮች ነበሩ።

እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ሰኔ 6፣ 1944 የተባባሪዎቹ ሐገራት ወታደሮች፣ ከአዉሮፕላን እየወረዱ ፈረንሳይን ይቆጣጠሩ ከነበሩ የጀርመን ጠላቶቻቸዉ ጋር የገጠሙት ዉጊያ ብዙ ሺሕ  ሠራዊት ያለቀበት፣ የቆሰለና የተማረከበት ግን የጦርነቱን የኃይል ሚዛን የቀየረ ዉጊያ ነበር።D-DAY ተብሎ የሚጠራዉ ዕለት የጀርመንን ሽንፈት፣ የተባባሪዎቹ ሐገራትን ድል ያመለከተ፣ አዲሲቱን አዉሮጳን የቀረፀ ተብሎም ይጠራል።ዕለቱን ምክንያት በማድረግ የፓሪሷ ወኪላችን ኃይማኖት ጥሩነሕን በስልክ አነጋግሪያታለሁ።

ኃይማኖት ጥሩነሕ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ 

Audios and videos on the topic