1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የናጎርኖ ካራባሕ ስደተኞች አርሜንያ እየገቡ ነዉ

ማክሰኞ፣ መስከረም 15 2016

የአርመኒያ ጠቅላይ ሚኒስተር ኒኮል ፓሺንቫንም፤ በአካባቢው የዘር ማጽዳት ዘምቻ ሊካሄድ እንደሚችል ለመገናኛ ብዙሀን መናገራቸው የተሰማ ሲሆን፤ እሳቸው ግን መንግስታቸው ያዘርባጃን አርመኖችን መካላከል በለመቻሉ ስልጣናቸውን እንዲለቁ እየተጠየቁ እንደሆነም ታዉቁል።

https://p.dw.com/p/4WpjR
የአርሜንያ ዝርያ ያላቸዉ የናጎርኖ ካራባሕ ነዋሪዎች እየተሰደዱ ነዉ
ከናጎርኖ ካራባሕ ወደ አርሜንያ የሚደረገዉ ስደትምስል Irakli Gedenidze/REUTERS

የናጎርኖ ካራባሕ ግጭትና ስደተኞች

አርሜኒያና አዘርበጃን በይገባኛል በሚወዛገቡበት በናጎርኖ ካራብክህ ግዛት የሚኖሩ የአርሜንያ ዝርያ ያላቸዉ ሰዎች አካባቢዉን ለቅቀዉ ወደ አርሜንያ እየተሰደዱ ነዉ።የአርሜንያ ዝርያዎች የሚኖሩበት የናጎርኖ ካራባሕ ግዛት በይፋ የአዘርበጃን ግምዳ-ግዛት አካል ቢሆንም ሁለቱ የቀድሞዊ ሶቭየት ሕብረት ሪፐብሊኮች በይገባኛል ይወዛገቡ፣ አንዳዴም ይጋጩበታል።በአርሜንያ መንግስት ይደገፋሉ የሚባሉ የናጎርኖ ካራባሕ አማፂያን በቅርቡ ባካባቢዉ ያሉ የአዘርበጃን መንግስት ባለስልጣናትን ገድለዋል በሚል የአዘርበጃን ጦር በከፈተዉ ጥቃት ናጎርኖ ካራባሕን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አስታዉቋል።የናጎርኖ ካራባክ ዉጊያ መዘዙ
እስካሁን 14 ሺ የሚሆኑ ድንበር አቋርጠው እንደገቡ ታውቁል። ድንበር አቁርጠው ወደ አርመኒያ ከገቡት ውስጥ አንዷ ለስደት የተዳረጉበትን ምክኒያት  ሲገልጹ፤ “ የተፈጠረው ሁኒታ የማይታመን ነው። መግለጫ ቃላት የለኝም። መንደሩ በከባድ መሳሪያ ተደብድቧል። አሁን በመንደሩ አንድም ሰው የለም” በማለት እዚያ ለመቆየት ምንም አይነት የህይወት ዋስትና አለመኖሩን ገልጸዋል። 
የአርመኒያ ጠቅላይ ሚኒስተር ኒኮል ፓሺንቫንም፤ በአካባቢው የዘር ማጽዳት ዘምቻ ሊካሄድ እንደሚችል ለመገናኛ ብዙሀን መናገራቸው የተሰማ ሲሆን፤  እሳቸው ግን መንግስታቸው ያዘርባጃን አርመኖችን መካላከል በለመቻሉ ስልጣናቸውን እንዲለቁ እየተጠየቁ እንደሆነም ታዉቁል። 
 

ናጎርኖ ካራባሕ የሚገኝ አንድ የታንክ ማከማቻ ሲቃጠል
የአዘርበጃን ጦር በከፈተዉ ጥቃት ናጎርኖ ካራባሕ ዉስጥ የተፈጠረዉ ቃጠሎምስል Siranush Sargsyan's Twitter account/AP/dpa/picture alliance

እ እ እ ከ1917ቱ የሩስያ አብዮት በኋላ፤ በ1923 አም ሶቭየቶች 95 ከመቶ ኑዋሪዎቹ አርመኖች የሆኑትን የናጎርኖ ካራባክ ግዝት በአዘርባጃን የሶቭየት ሪፑብሊክ ስር አድርገውት ቆይተዋል።  እ እ በ1991 ዓም የሶቭየት ህብረት መፍረስንና የአዘርባጅንና አርመኒያ በየራስቸው መንግስት መሆንን ተክትሎ ግን ናጎርኖካራባክምም የራሱን ነጻነት አውጆ የነበር ሲሆን፤ ይህም በአዘርባጃንና አርመኒያ በተደጋጋሚ ጦርነት ውስጥ መግባት ዋና ምክኒያት ሁኖ ቆይቷል። እ እ እ በ1994 አም የሚኒስክ ቡድን የሚባልና ሩሲያ ፈረንሳይና አሜርካ ያሉበት ሸምጋይ ቡድን ተቋቁሞ የነበር ቢህንም፤ እሳክሁንም ግን ለአክባቢው ዘላቂ ሰላም ሳያመጣ ነበር የቆየው። ባለፈው ሳምንት ግን አዘርባጃን አሸባሪዎች በሚላቸው የአካባቢው ታጣቂዎች ላይ በከፍተው ወታደራዊ ዘመቻ፤ በአርመኖቹ መስተዳድርና ተቋሞቻቸው ላይ ጥቃት ማድረሱ የተገለጸ ሲሆን፤ በመጨረሽም ከታጣቂ ቡድኑ ጋር የተኩስ ማቆም ስምምነት እንደተደረሰ ተገልጿል። በመገናኛ ብዙሀን  እንደተገልጸውም ታጣቂው ቡድን ከ20 ሺ በላይ ተተኳሾች፣ 6 የጦር ተሽከርክሪዎችንና  ከ800 በላይ ቀላልና ከባድ መሳሪያዎችን አስረክቧል ።የተመድ 75ኛ ጠቅላላ ጉባኤና ግጭቶች 
 
አዘርባጃን ለምን በዚህ ወቅት ይህን እርምጃ ወሰደች ለሚለው ጥያቄ የመክላከያና ደህንነት ተመራማሪው ፕሮፌሰር ሚኬል ክላርክ ሲመልሱ፤ “ አስር ሚሊዮን ህዝብ ያላትና የነዳጅና ጋዝ ባለጸጋ የሆነችው አዘርባጅን ሶስት ሚሊዮን ህዝብ ካላት አርመኒያና 120ሺ ኑዋሪዎች ክሉት ናጎርኖ ክራባክ አንጻር ጉልበተኘነት ሊሰማት ይችላል። በዚያ ላይ ላይ አሁን አዳዲስ ቴክኖጂዎችን አግንታለች፤ ከቱርክ ጋርም የጠበቀ ግንኑነት አላት በማለት በዚህም ምክኒያት አሜሪካና ብሪታኒያም በአካባቢው ያላቸውን የመከላከያ ፖሊሲ ስይቀይሩ እንዳልቀሩ ገልጸዋል። 
 
የአዘርባጃን መንግስት ግን  ናጎርኖ ካርባክ የሚኖሩ አርመኖች ቁንቋቸውንና ባህላቸውን አስጠብቀው የአዘርባጃን ዜጎች ሆነው እንደሚኖሩና ለዚህም በስፋት እየሰራ እንደሆነ እየገለጸ ነው። የአዘርባጃን መካለክያ ሚኒስተር ቃል አቀባይ ሚስተር አናር ኤይቫዞቭ ሲናገሩ እንደተሰሙት፤ “ ሰራዊቱ ከሩሲያ የሰላም አስከባሪ ሀይል ጋር በመተባበር አካባቢውን ከወታደራዊ ቀጠናነት በማጽዳት ሰላማዊ ሰዎችን በመርዳት ላይ ነው።” ይሁን እንጂ የአዘርባጃን መንግስት እየገለጸ ካለውና እየሰጠ ካለው ዋስትና ውጭ የአርመኖቹ ስጋትና ችግርም ክፍተኛ እንደሆነ  ነው የሚነገረው። ከዚህ አንጻር የአውሮፓ ህብረትና አባል መንግስታቱ ጉዳዩን በቅርብ እንደሚከታተሉትና ድጋፍም እንደሚይደርጉ የገልጹ ሲሆን የአሜሪካ መንግስት ሉዕክም ወ ደአርመኒያ ተጉዞ ከአርመኒያ መንግስት ጋር መምከሩ ተዘግቧል። በዛሬው እለት የአውሮፓ ህብረት ለናጎርኖ ካራብክ ስደተኖች ተጨማሪ መርጃ 5 ሚሊዮን ኢሮ መለገሱንም አስታውቋል። 

የሁለቱ ሐገራት መሪዎች ዘላቂ ሰላም አላወረዱም
ከግራ ወደ ቀኝ የአዝርበጃን ፕሬዝደንት ኢልሐም አልዬቭና የአርሜኒያ ጠቅላይ ሚንስትር ኒኮል ፓሺንያንምስል GENT SHKULLAKU/AFP

ገበያው ንጉሤ

ነጋሽ መሐመድ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር