የናዚ ዕስርቤቶች ቁጥር ጨምሯል | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 30.07.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የናዚ ዕስርቤቶች ቁጥር ጨምሯል

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ናዚዎች ሰዎችን ያሰቃዩ ያንገላቱባቸው እና ይገድሉባቸው የነበሩ እስር ቤቶች ብዛት ከዚህ ቀደም ይገመት ከነበረው በላይ ከፍተኛ ሆኖ መገኘቱን ባለፈው ሰሞን ይፋ የሆነ አንድ የጥናት ውጤት አስታውቋል ።

default

የአውስሽቪትዙ የህዝብ ማጎሪያ እና ማሰቃያ ማዕከል

ጥናቱ እንደሚለው በጀርመንና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ናዚዎች በኃይል በያዙዋቸው አገሮች ውስጥ ከሀያ ሺህ በላይ የናዚ የእስረኞች ማጎሪያ ሰፈሮች እንደነበሩ ተደርሶበታል ። የዛሬው ዝግጅታችን ከሚመለከታቸው ርዕሰ ጉዳዮች አንዱ ነው ። ከዚሁ ከጀርመን ሳንወጣ በጀርመን አስጊ የሆነው የአስተማሪዎች ዕጥረት እንዲሁም በጀርመን የሚወለዱ ልጆች ቁጥር እየቀነሰ መምጣት በዛሬ ቆይታችን ተካተዋል ።

ሂሩት መለሰ