1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የናሚቢያዉ ቁስል እስኪሽር ረጅም ጊዜ ይወስዳል

ቅዳሜ፣ ግንቦት 21 2013

የጀርመን መንግሥት ከ 100 ዓመታት በፊት የጀርመን ቅኝ ገዢ ጦር በዛሬዋ ናሚቢያ በሔሬሮ እና ናማ ጎሳዎች ላይ የፈጸመዉ ወንጀል «ጅምላ ግድያ» ነዉ ስትል መቀበልዋን በተመለከተ ሃተታ።

https://p.dw.com/p/3u9UD
Überlebende Herero nach der Flucht durch die Wüste
ምስል public domain

እርቁ የሚጀምረዉ ስለተጎዱት ሰዎች በጋራ ሲሰራ ነዉ

ጀርመን በስተመጨረሻ በሄሬሮ እና ናማ ላይ የደረሰዉን ወንጀል ዘር ማጥፋት ስትል ኃላፊነትን ወስዳለች። በስተመጨረሻም የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ምዕራብ አፍሪቃዊትዋ ሃገር ላለፉት 100 ዓመታት ስትጠብቀዉ የነበረዉን ቃል ይናገሩታል። በስተመጨረሻም በጀርመኖች የተፈፀመ ጭካኔ የተሞላበትን ወንጀል፣ ጀርመን አልደብቅም አቃልዬ አላይም፤ ዉይም ችላ ለማለት አልሞክርም ብላለች። በጀርመናዉያኑ ዘንድ ይህ ትልቅ እርምጃ ነዉ። በናሚቢያ ግን ሌላ ትርጉም ያለዉ ይመስላል። የናሚቢዉ  ፕሬዚዳንት ለስለስ ባለ የዲፕሎማሲ ቋንቋ  «ርምጃዉ ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ እያመራነዉ» ሲሉ ነዉ መልስ የሰጡት።  

Pelz Daniel Kommentarbild App
ሃተታ በዳንኤል ፔልዝ

የተናደዱት የሄሬሮ ተወካዮች

አንዳንድ የሄሬሮ የናማ ኅብረተሰብ ባህላዊ መሪዎች እንዲሁም የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት፤ ጀርመን ለዘር ማጥፋቱ ወንጀል በናሚቢያ የትምህርት ቤት እና የተለያዩ መሰረተ ልማት ግንባታን በማካሄድ ካሳ ለመክፈል ማቀድዋ አስቆጥቶአቸዋል፤ የሚሳደቡም አሉ። ጉዳዩን በሌላ መልክ ቀይረዉ የሚያወሩም ጥቂቶች አይደሉም። ምክንያታቸዉ ደግሞ ይፈፀማል የተባለዉ የተለያየ የመሰረተ ልማት ግንባታ በግልፅ ባለመቀመጡ፤ ጀርመን ለናሚቢያ መሰረተ ልማቶቹን ስታስገነባ በስጦታ ያቀረበች ይመስላታል ሲሉ በመዉሰዳቸዉ ነዉ። እንድያም ሆኖ ግን ጀርመን ልታስገነባዉ ያቀደችዉን መሰረተ ልማቶች በተመለከተ፤ መሰረተ ልማቱ ይገነባል ብለዉ የሚሚያምኑ የናማም ሆነ የሄሬሮ ማኅበረሰብ አባላት ጥቂት የሚባሉ አይደሉም። ቢሆንም አብላጫዉን ቁጥር የሚይዘዉ የሚያምነዉ አልያም የማያምነዉ ማኅበረሰብ ስለመሆኑ እስካሁን በግልፅ የሚታወቅ ነገር የለም።    

አሁን በአብዛኛዉ ኃላፊነት የወደቀዉ በሁለቱ ሃገራት መንግሥታት ጫንቃ ላይ ነዉ።  የእርቅ ጥያቄዉም ተገቢ የሚሆነው በአብዛኛዉ ናሚቢያዜጋ ከተቀበለዉ ብቻ እና ክንዉኑም የሚፈፀመዉ በመተማመን ከሆነ ነው። በናሚቢያ ፓርላማ ንግግር እንደሚያደርጉ የተነገረዉ የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክቫልተር ሽታይንማየር በንግግራቸዉ ጥሩ ቃላትን እንዲያገኙ መልካሙን እንመኛለን። በሄሬሮ እና በናማ ማኅበረሰብ ላይ የተካሄደዉ የዘር ፍጅት መፈፀሙን በተመለከተ በናሚቢያ ፓርላማ ከሚካሄደዉ  የይቅርታ መጠየቅ ሥርዓት በተጨማሪ በተጎጂዎች መታሰብያ ቦታ ይህ ሥነ-ስርዓት መካሄዱ አስፈላጊ ነዉ። ከዛ የካሳዉ ጉዳይ ይጀምራል።    

እርቁ የሚጀምረዉ የጀርመን ትምህርት ቤቶች በመጻህፍቶቻቸዉ እና በስርዓተ-ትምህርቶቻቸዉ ጭፍጨፋውን ሳይደብቁ ጊዜ ሰጥተዉ ሲማሩበት እና ሲነጋገሩበት ነዉ። እርቁ የሚጀምረዉ የጀርመን ቱሪስቶች በናሚቢያ በቅኝ ግዛት ዘመን የተገነቡትን ህንፃዎች ብቻ ሳይሆን ከህንጻዉ ጀርባ ያለዉን አስከፊ ታሪክ ሲረዱና ሲጎበኙት ነዉ። በናሚቢያ የጀርመናዉያን ታሪክ የጀርመን መንግሥት እና ባለስልጣናት ብቻ ሳይሆኑ እርቁ የሚጀምረዉ አብዛኛዉ ጀርመናዊ አዎ ጥቁር ታሪክ ብሎ የታሪኩን አስከፊነት ሲረዳ ነዉ። እርቁ የሚጀመረው የናሚቢያ ህዝብ በተለይም የሄሬሮ እና የናማ ብሔረሰቦች ጀርመን ይቅርታ ስትጠይቅ እዉነትዋን ነዉ ብለዉ ሲያጤኑ እና ሲቀበሉት ነዉ። እርቁ የሚጀምረዉ ጀርመናዉያን እና ናሚቢያዉያን ስለተጎዱት ሰዎች በጋራ ሲያዝኑ ነዉ። ግን ይህ ሁሉ ሂደት እስከሚከሰት ገና ብዙ መጓዝን ይጠይቃል። 

አዜብ ታደሰ / ዳንኤል ፔልዝ