የኒጀር መፈንቅለ መንግስት | ኢትዮጵያ | DW | 19.02.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኒጀር መፈንቅለ መንግስት

ምዕራብ አፍሪቃዊቷ አገር ኒዠር ትናንት በመፈንቅለ መንግስት አዙሪቷ ዳግም ገብታለች።

default

በኃይል የተወገዱት ማማዱ ታንጃ

አገሪቱ ነፃነቷን ካገኘች ወዲህ ለኒዠር ስድስተኛዉ ፕሬዝደንት ማማዱ ታንጃ በወታደራዊ ኹንታ ከመንበራቸዉ ተነስተዉ በቁጥጥር ስር ዉለዋል። ታንጃ በቀጣይ ስልጣን መንበራቸዉ ላይ ለመሰንበት የአገሪሩን ህገመንግስት ማሻሻላቸዉ ከመነቀፍ ባሻገር ለዚህም እንዳበቃቸዉ ይገመታል። የአፍሪቃ ኅብረት፤ የምዕራብ አፍሪቃ አገራት የምጣኔ ሃብት ማኅበረሰብ ECOWAS በኒዠር የተካሄደዉን የመንግስት ግልበጣ አዉግዘዋል። ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት የኒዠር ዋና ከተማ ናያሚ ዛሬ ተረጋጋግታለች፤ ህዝቡም የወትሮ ተግባሩን ቀጥሏል።

ሸዋዬ ለገሠ/አርያም ተክሌ