የኒውክለር ሃይልና የአከባቢ ጥበቃ | ጤና እና አካባቢ | DW | 15.03.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

የኒውክለር ሃይልና የአከባቢ ጥበቃ

ጃፓን በርዕደ መሬት ከተመታች በኋላ የተከሰተው የኒውክለር አደጋ በአከባቢና በጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል።

default

ጃፓን ብርቱ አደጋ ከገጠማት ዛሬ አምስተኛ ቀኗን ያዘች። ያለፈው ዓርብ ጠዋት የደረሰው ርዕደ መሬት በ140 ዓመት ታሪኳ የመጀመሪያው ከባድ አደጋ ሆኖ ተመዝግቧል። በዓለም ከተከሰቱት 7 ከፍተኛ መጠን ያለው ርዕደ መሬት አንደኛው መሆኑም ይነገራል። በእርግጥም ያለፈው ዓርብ ጃፓን የገጠማት ዱብ እዳ ድንገተኛና አስደነጋጭ ነበር።

ሰላም ጤና ይስጥልን። ጃፓን የደረሰው የርዕደ መሬት አደጋ ሌላ ግዙፍ ችግር ፈጥሯል። በኒውክለር ጣቢያዎቿ ላይ ተከታታይ የሆነ ፍንዳታ ተከስቶአል። ኒውክለርን ለሃይል ማመንጪያነት በመጠቀም ጃፓን አንደኛዋ ሀገር ሆና ትጠቀሳለች። ከሌሎች የሃይል ማመንጪያ መንገዶች ማለትም ከውሃ፤ ከንፋስ፤ ከጸሃይ ብርሃንና ከጂኦተርማል ማመንጪያዎች ከካርበን ነጻ የሆነ ሃይል የሚገኘው ከኒውከለር ነው። ይህም የአከባቢ ብከለት የማያስከትል አማራጭ ተደርጎ እንዲወሰድ ያደርገዋል። ይሁንና ሰሞኑን ጃፓን የተከሰተው የኒውክለር ፍንዳታ በአከባቢና በጤና ላይ ተጽእኖ እያስከተለ እንደሆነ ከስፍራው እየተሰማ ነው። ለመሆኑ የኒውክለር ሃይል በአከባቢና በጤና ላይ የሚኖረው ተጽእኖ ምንድን ነው? ከአማራጭ የሃይል ምንጮች አንጻር የተጽእኖው መጠን ምን ያህል ነው? የዕለቱ ጤናና አከባቢ ፕሮግራም የኒውክለር ሃይል በአከባቢና በጤና ላይ የሚኖረውን ተጽእኖ ይቃኛል። የጃፓን ሰሞንኛ አደጋን መነሻ አድርገን ከባለሙያ ማብራሪያ ጋር ጥቂት ጊዜ አብረን እንቆያለን። ለዝግጅቱ መሳይ መኮንን ነኝ።

መሳይ መኮንን

ነጋሽ መሀመድ