የኑሮ ውድነት በባሕር ዳር ከተማና አካባቢዋ | ኢትዮጵያ | DW | 24.08.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኑሮ ውድነት በባሕር ዳር ከተማና አካባቢዋ

ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የዋጋ ንረት ሯቸውን ለመምራት እንዳላስቻላቸው የባህር ዳርና አካባቢው ነዋሪዎች በመግለጥ አማረሩ። መንግስት በበኩሉ ያለ አግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ  የማያዳግም ርምጃ እወስዳለሁ ብሏል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:53

በኑሮ ውድነቱ በርካቶች ተማረዋል

ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የዋጋ ንረት ሯቸውን ለመምራት እንዳላስቻላቸው የባህር ዳርና አካባቢው ነዋሪዎች በመግለጥ አማረሩ። መንግስት በበኩሉ ያለ አግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ  የማያዳግም ርምጃ እወስዳለሁ ብሏል። ከወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ጋርም ይሁን በሌላ ምክንያት የምግብ ምርትና የሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ፤ በተለይም በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችን በእጅጉ እየጎዳ እንደሆነ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬሌ የተናገሩ ነዋሪዎች አመልክተዋል።

የዋጋ ጭማሪው በፍራፍሬ ላይ ሳይቀር በአስደንጋጭ ሁኔታ እያደገ መምጣቱን ነው ወ/ሮ ሙሉ የሚናገሩት። አንዳንድ ነጋዴዎች ወቅታዊ ጉዳዩን እንደመልካም አጋጣሚ ቆጥረውታል ባይ ናቸው አስተያየት ሰጪዋ።

ከባሕር ዳር 40 ኪሎሜትር ያክል ከምትርቀውና በምርታማነት ከምትታወቀው አዴት አካባቢ አስተያየት የሰጡን ነዋሪም ኑሮ አስቸጋሪ መሆኑን ነው የገለፁት። የገበያ ጥናት ባለሙያ ወ/ሮ ፀጋ ዳኝነት የዋጋ ጭማሪው በየሳምንቱ እጨመረ ነው። 

ችግሩን ለማቃለልል ዩኒዮኖችና ህብረት ስራ ማህበራት ምርት በማሰባሰብ በተመጣጣን ዋጋ ለህብረተሰቡ የማድረስ ስራ እንደሚሰራ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መለስ መኮንን ሰሞኑን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ አግባብነት የሌለው የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች የማያዳግም ርምጃ ይወሰድባቸዋል።

ዓለምነው መኮንን  
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች