የነፃነት ታጋዮ ከእስር ነፃ የሆኑበት 30ኛ ዓመት | አፍሪቃ | DW | 08.02.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የነፃነት ታጋዮ ከእስር ነፃ የሆኑበት 30ኛ ዓመት

እዉቁ የነጻነት ታጋይ የደቡብ አፍሪቃዉ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ ፤ ከ 27 ዓመታት እስራት በኋላ ነፃ የወጡበት 30 ኛ ዓመት የፊታችን ማክሰኞ ይታሰባል። ኔልሰን ማንዴላ የዛሬ 30 ዓመት የካቲት 3 ቀን 2012 ዓ.ም በጎርጎረሳዉያኑ የካቲት 11 ነበር ከእስር ነፃ የሆኑት።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:36

የካቲት 3 ቀን 2012 ዓ.ም ማንዴላ ከእስር የተፈቱበት 30 ዓመት

እዉቁ የነጻነት ታጋይ የደቡብ አፍሪቃዉ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ ፤ ከ 27 ዓመታት እስራት በኋላ ነፃ የወጡበት 30 ኛ ዓመት የፊታችን ማክሰኞ ይታሰባል። ኔልሰን ማንዴላ የዛሬ 30 ዓመት የካቲት 3 ቀን 2012 ዓ.ም በጎርጎረሳዉያኑ የካቲት 11 ነበር ከእስር ነፃ የሆኑት። ደቡብ አፍሪቃን ከአፓርታይድ ስርዓት ያላቀቀዉ እና የኔልሰን ማንዴላን ከእስር እንዲወጡ ያደረገዉ የበርካታ አፍሪቃ ሃገሮች የትግልና የመስዋዕትነት ዉጤት ነበር። ይሁንና ዛሬ ዛሬ በደቡብ አፍሪቃ የሚታየዉ ዘረኝነት እና የሌላ አፍሪቃ ዜጋን ጠለነት ብዙዎችን አፍሪቃዉያንን የሚያሳስብ ሆንዋል። አፓርታይድ ከመገርሰሱ በፊት የነበሩት የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚዳንት ዲክለርክ ፤ በፓርላማቸዉ መድረክ ወጥተዉ ሚሊዮኖችን ያስፈነደቀዉን ፤ ግን ደሞ ጥቂት የማይባሉትን ያስደነገጠዉ እና ያስቆጣዉንም ንግግር ያደረጉት በጎርጎረሳዉያኑ 1990 ዓ.ም  እንደነበር ይታወሳል። ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ!

 

ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic