የኅዳር 09 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
ሰኞ፣ ኅዳር 9 2017በአውሮጳ የኔሽንስ ሊግ የእግር ኳስ ግጥሚያዎች ጀርመን እና እንግሊዝ ተጋጣሚዎቻቸውን የግብ ጎተራ አድርገው ሸንተዋል ። በአውሮጳ እጅግ ገናና ከሆኑት ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የቤልጂየም ቡድን በተጋጣሚው የእሥራኤልን ቡድን ድል ተነስቷል ። የ58 ዓመቱ የከባድ ሚዛን ቡጢኛ ማይክ ታይሰን ከ27 ዓመቱ ተፋላሚ ጋር መጋጠሙ የሳምንቱ መጨረሻ መነጋገሪያ ሁኑ ሰንብቷል ።
አትሌቲክስ
የ2024 የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድሮች በትናንትናው ዕለት አዲስ አበባ ውስጥ ተከናውነዋል ። በዓለም አቀፍ 10 ኪ.ሜ የሴት እና የወንዶች ፉክክር፦ አትሌት ቢንያም መሐሪ 00:28:25.661 ሰከንድ በመሮጥ አሸናፊ ሁኗል ። አትሌት አዲሱ ነጋሽ እና ይስማው ድሉ ከቢንያም በከአንድ እና አራት ደቂቃ ተከታትለው በመግባት ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ አግኝተዋል ።
በሴቶች ተመሳሳይ ፉክክር ደግሞ፦ የንግድ ባንክ አትሌት አትሌት ዐይቼሽ ዐይቸው ውድድሩን በ00:32:13.4 በማጠናቀቅ አንደኛ ደረጃ አግኝታለች ። ከአሸናፊዋ ዐይቼሽ በመከተል የቡድን አጋርዋ አትሌት የኔዋ ንብረት እና ቦሰና ሙላት ሁለተኛ እና ሦስተኛ ወጥተዋል ። ሁለቱም ከዐይቼሽ የተቀደሙት በሦስት እና ዐሥራ አራት ሰከንዶች ልዩነት ነው ።
እግር ኳስ
ሞሮኮ በምታሰናዳው የ2025 የአፍሪቃ ዋንጫ ማጣርያ 5ኛ የምድብ ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡድን በታንዛንያ የ2 ለ0 ሽንፈት ገጠመው ። የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኪንሻሳ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ስታድ ደ ማርትየርስ በተደረገው የቅዳሜው ግጥሚያ ለታንዛኒያ ሁለቱን ግቦች ያስቆጠሩት ሲሞን ምሱቫ እና ፋይሳል ሳሉም ናቸው ። ኮትዲቯር አላሳን ዋታራ ኢቢምፔ ስታዲየም ውስጥ ትናንት በነበረ ሌላ የማጣሪያ ግጥሚያ፦ ኮንጎ ውስጥ በነበረ ሌላ ግጥሚያ ደግሞ፦ ጊኒ በባከነ ሰአት የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን 1 ለ0 አሸንፋለች ። ለጊኒ የማሸነፊያዋን ግብ መደበኛው ዘጠና ደቂቃ ተጠናቆ በጭማሪው 2ኛ ደቂቃ ላይ ከመረብ ያሳረፈው የቦሩስያ ዶርትሙንዱ አጥቂ ሴህሩ ጊራሲ ነው ። የቅዳሜው ድል ጊኒን በ9 ነጥቦች ከምድቡ የሁለተኛ ደረጃ አስገኝቶላታል ። በስምንት ተከታታይ የማጣሪያ ግጥሚያዎቹ አንድም ግብ ሳይቆጠርበት ዘልቆ የነበረው የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ቡድን በሳምንቱ መጨረሻ ላይ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል ። ባለፈው የአፍኮን ውድድር አራተኛ ደረጃ ያገኘው የኮንጎ ቡድን በወቅቱ ጊኒን ከሩብ ፍጻሜው ማሰናበቱ የሚታወስ ነው ። ኢትዮጵያን ያሸነፈችው ታንዛኒያ 7 ነጥብ ሰብስባ ከምድቡ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ። የኅዳር 02 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
ነገ ዳር ኤ ሣላም ውስጥ በሚደረገው ግጥሚያ ከጊኒ እና ታንዛኒያ አሸናፊዎች አንዱ በቀጥታ ለአፍሪቃ ዋንጫ ከሚያልፉ ቀሪ አምስት ሀገሮችን ይቀላቀላሉ ። ዛሬ እና ነገ በሚኖሩ 11 የመጨረሻ የማጣሪያ ግጥሚያዎች ከ24ቱ ተሳታፊ ሃገራት አምስቱ ይለያሉ ። እስካሁን በነበሩ ግጥሚያዎች 11 ግቦች የተቆጠሩበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አንድ ግብ በማስቆጠር ባገኘው አንድ ነጥብ ብቻ ተወስኖ ከምድቡ የመጨረሻ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ።
የኔሽን ሊግ ግጥሚያዎች
የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በኔሽን ሊግ ግጥሚያ ቦስኒያ ሔርዞጎቪና ላይ 7 ግቦችን በማስቆጠር የግብ ጎተራ አደረገ ። በቅዳሜው ግጥሚያ ጃማል ሙሳይላ ድንቅ ብቃቱን አስመስክሯል ። ጃማል የተጋጣሚው ክልል ውስጥ ዘልሎ ኳሷን በጭንቅላት ገጭቶ ከመረብ ሲያሳርፍ ጨዋታው ከጀመረ 79 ሰከንድ ብቻ ነበር የተቆጠረው ። በቀኝ በኩል በድንቅ ሁኔታ ኳሷን ያሻማው ጆሹዋ ኪሚሽ ነው ። ከዚህ ዐይን ገላጭ አስደንጋጭ ግብ በኋላ የቦስኒያ ሔርዞጎቪና ተጨዋቾች መላው ነበር የጠፋቸው ። 23ኛው እና የማሳረጊያዋን ሰባተኛ ግብ 79 ደቂቃ ላይ ቲም ክላይንዲንስት፤ በ37ኛው ደቂቃ ካይ ሐቫርትስ፤ በ50 እና 57ኛው ደቂቃ ፍሎሪያን ቪርትስ እንዲሁም ሌሮይ ሳኔ 66ኛ ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፈዋል ።
ከናይጀሪያዊ አባት እንዲሁም ከጀርመን እና ፖላንድ የዘር ሐረግ ከተገኙ እናት የተወለደው ጃማል ሙሳይላ የቡድኑ ኩራት ሁኖ አምሽቷል ። የ21 ዓመቱ ወጣት ጃማል እስካሁን ለ177 ጊዜያት ተሰልፎ ተጫውቷል ። ጀርመን በኔሽንስ ሊግ ግጥሚያ ምድቡን በ13 ነጥብ ይመራል። ኔዘርላንድስ በ8 ይከተላል ። ሐንጋሪ በ5 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ሲይዝ፤ ቦስኒያ ሔርዞጎቪና በ1 ብቸኛ ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ።
በሌሎች ምድቦች በመሪነት ከሰፈሩት መካከል፦ ፖርቹጋል፤ ስዊድን፤ ኖርዌይ፤ ስፔን እና ፈረንሳይም 13 ነጥብ አላቸው ። ጣሊያን 2ኛ ብትሆንም እንደ ፈረንሳይ ሁሉ 13 ነጥብ አላት ። ሰሜን መቄዶንያ ሊግ ሐ ውስጥ በሚካሄደው ፉክክር በ16 ነጥብ መሪ ናት ። በሊግ ለ መሪው እንግሊዝ እና ግሪክ ከምድባቸው ሁለቱም 15 ነጥብ ሰብስበዋል ። ሮማኒያ በ12፤ ቱርኪዬ በ11፤ ሰሜን አየርናልድ በ10፤ ሞልዶቫ በ9፤ ቼክ ሪፐብሊክ 8፤ ጂብራልታር በ6 ነጥብ የየምድባቸው መሪዎች ናቸው ።
የጥቅምት 25 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በነበሩ ግጥሚያዎች ኔዘርላንድስ ሐንጋሪን 4 ለ0፤ ኖርዌይ ካዛክስታንን እንዲሁም እንግሊዝ አየርላንድን 5 ለ0 አሸንፈዋል ። ቤልጂየም ትናንት በያርዴን ሹዋ ብቸኛ ግብ በእሥራኤል 1 ለ0 መሸነፏም መነጋገሪያ ሁኗል ። ከዚያ ቀደም ብሎ አምስተርዳም ውስጥ የማካቤ ቴል አቪቭ እና አያክስ አምስተርዳም ቡድኖች ግጥሚያ ወቅት የእሥራኤል ደጋፊዎች እና የፍልስጥኤም ሰልፈኞች ተጋጭተዋል ። ጸረ ሴማዊ ጥላቻ ተቀስቅሶ በደጋፊዎች መካከል ግጭት ታይቷል ። እሥራኤል ከፈረንሳይ ጋ 0 ለ0 በተለያየችበት የሐሙሱ ግጥሚያ ደግሞ ፓሪስ ውስጥ ጥበቃው እጅግ ተጠናክሮ ነበር ። የሁለቱ ቡድኖች ደጋፊዎች ረብሻ ሊካረር ሲል ፖሊስ በመሀል ገብቶ አረጋግቷል ። የፍልስጥኤም ደጋፊዎች ተቃውሞ ሰልፎችም ታይተዋል።
ቡጢ
ላለፉት 20 ዓመታት ፕሮፌሽናል የቡጢ ግጥሚያዎችን ያላከናወነው የ58 ዓመቱ ማይክ ታይሰን ከዩቲዩበርነት ወደ ቡጢ ስፖርት ከተሻገረው የ27 ዓመቱ ጃክ ፖል ጋር ያደረገው ግጥሚያ እጅግ መነጋገሪያ ሁኗል ። ሁለቱ ቡጢኞች ዳላስ በሚገኘው አዳራሽ 70,000 ታዳሚ ፊት ያደረጉት ግጥሚያ ብዙ ጥያቄዎችን አጭሯል ። ውድድሩን ሚሊዮኖች ኔትፍሊክስ በተባለው የፊልም እና ስፖርት መመልከቻ አውታር በቀጥታ ተከታትለዋል ።
ውድድሩን ለመመልከት በዓለም 60 ሚሊዮን ሰዎች ኔትፍሊክስ ከፍተው እንደነበረም ተዘግቧል ። ፓል ውድሩን 120 ሚሊዮን ሰዎች መመልከታቸውን ተናግሯል ። በውድድሩ ፍጻሜ በሰጠው ቃለ መጠይቅም፦ «አድናቂዎቼን ማዝናናት ፈልጌያለሁ ግን ደግሞ መጎዳት የሌለበትን ሰው መጉዳትም አልፈለግሁም ነበር» ብሏል ። አንዳንዶች ፓል ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ቢጋጠም ማይክ ታይሰንን እጅግ ሊጎዳው ይችል ነበር ሲሉ ተደምጠዋል ። «ተሸንፈህም እንዳሸነፍህ» ይቆጠራል ያለው ማይክ ታይሰን በበኩሉ፦ «ባለፈው የቡጢ መድረኩ ውስጥ በመግባቴ አልጸጸትም» ሲል ተደምጧል ። የጥቅምት 18 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
ጀርመን የሚኖሩት የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ዶክተር ጸጋዬ ደግነህ የጀርመን ጁ ጂትሱ ፌዴሪሽን የ6ኛ ዳን ዲግሬ ጥቁር ቀበቶ የሆነው የግራንድማስተር ማዕረግ ባለቤት ናቸው ። የማይክ ታይሰን እና የጃክ ፖልን ግጥሚያ እንዴት ተመለከቱት? ከስፖርታዊ ስነምግባር አንጻር እንዴት ይታያል? እንደ ጁ ጂትሱ እና ካራቴ ባሉ የስፖርት ዘርፎችስ እንዲህ ከፍተኛ የዕድሜ ልዩነት ያለው ግጥሚያ የተለመደ?
ስፔናዊው የዓለማችን ምርጥ የሜዳ ቴኒስ ተጋጣሚ የ38 ዓመቱ ራፋኤል ናዳል በዳቪድ ካፕ ፍጻሜ ከውድድሩ ዓለም እንደሚሰናበት ይፋ ሆነ ። ራፋኤል ናዳል በውድድር ዘመኑ 92 ጊዜያት ለድል በቅቷል ። ራፋኤል ናዳል ብዙ ጊዜያት ለፍጻሜ ድል የበቃው በፓሪስ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ዋና ዋና የፍጻሜ ግጥሚያዎች ለድል በቅቷል ። በአውስትራሊያ የሜልቦርን ፍጻሜ እና በዊምቤልደን ፍጻሜ በሁለቱም ለሁለት ጊዜያት አሸንፏል ። በኒው ዮርክ ፍጻሜ ደግሞ ለአራት ጊዜያት አሸናፊ መሆን ችሏል ። ራፋኤል ናዳል በስተመጨረሻ ማላጋ ውስጥ ነገ በሚያደርገው የዳቪስ ካፕ ፍጻሜ ውድድር የሜዳ ቴኒስ መሠረቢያውን በ38 ዓመቱ ይሰቅላል ማለት ነው ።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ታምራት ዲንሳ