የኅዋ ሳይንስ ሊቁ ዶ/ር ለገሰ ወትሮ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 28.04.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የኅዋ ሳይንስ ሊቁ ዶ/ር ለገሰ ወትሮ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኅዋ ሳይንስ ተመራማሪ፤መምህር እና የራዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ ዶ/ር ለገሰ ወትሮ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተፈጸመ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:42

የኅዋ ሳይንስ ሊቁ ዶ/ር ለገሰ ወትሮ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈጸመ

 በቀድሞ አጠራር በአሩሲ ክፍለ ሀገር ስሬ ወረዳ በ1942 ዓ.ም የተወለዱት ዶ/ር ለገሰ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን እና የማስተርስ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በፊዚክስ ትምህርት አግኝተዋል፡፡በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ድረ-ገፅ ላይ የሰፈረው መረጃ እንደሚጠቁመው ዶ/ር ለገሰ ከብሪታንያዉ ሼፊልድ ዩኒቨርሲ  በድጋሚ በፊዚክስ የማስተርስ ዲግሪ እንዲሁም ከአሜሪካው የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ አስትሮፊዚክስን በፒ.ኤች.ዲ አጥንተዋል። ዶ/ር ለገሰ የአፍሪቃ አስትሮኖሚ እንዲሁም የፊዚክስ ማህበራት አባል ነበሩ። በዓለም አቀፉ አስሮኖሚካል ሶሳይቲም በአባልነት አገልግለዋል።

ከተማሪዎቻቸው እና የሙያ ባልደረቦቻቸው ጋር የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲን የመሰረቱት የኅዋ ሳይንስ ሊቅ በራዲዮ እና ጋዜጦች ውስብስብ የሆነውን የኅዋ አፈጣጠር የሚተነትኑ ፅሁፎች እና የራዲዮ መሰናዶዎች በማቅረብም ይታወቁ ነበር። ከልብ ጋር የተገናኘ ሕመም የነበረባቸው ዶ/ር ለገሰ በመኖሪያ ቤታቸው በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል። በተወለዱ በ67 ዓመታቸው ያረፉት ዶ/ር ለገሰ የአንድ ወንድና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡ የዶ/ር ለገሰ ወትሮ ስርዓተ ቀብር ሚያዝያ ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘዉ በጴጥሮስ-ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈፅሟል።

 ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር 

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic