የኅዋ ምርምር ጠቀሜታ ለምድር | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 25.06.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የኅዋ ምርምር ጠቀሜታ ለምድር

ኢትዮጵያ፤ ከባሕር ልክ በታች 120 ሜትር ዝቅ ካለው ቦታ አንስቶ 4,620 ሜትር ከፍታ እስካለው ሥፍራ ፣ የሚያቃጥል የቀን ሐሩር ፣ የሚያኮማትር የሌሊት ቁር ፣ እንዲሁም ለዘብ ያለ የአየር ጠባይ ያላት ሀገር በመሆኗ ፤ ላገር ጎብኝዎች መስሕብነት

እንዳላት በየጊዜው ነው የሚነገረው። በተፈጥሮ ካላት ልዩ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥና ጥንታዊ ታሪካዊ ቅርሶች ሌላ፣ ሕዋን ሰንጥቆ ፣ የሰማይ አካላትን ፣ ከዋክብትን ፣ ፕላኔቶችንና የመሳሰሉትን ለማሰስ ፣ በአጭሩ ለሥነ ፈለክ ምርምርም ተስማሚ መሆኗ ይነገራል።

10 ዓመት የሆነው የኢትዮጵያ የኅዋ ሳይንስ ድርጅት፣ እንዲሁም ኅዋንና የሰማይ አካላትን መከታተያው፣ የኅዋ ጥናት ጣቢያ የሚያከናውኑት ተግባር በቀጣዩ ዝግጅት ተካቷል።ሳይንስና ሥነ ቴክኒክን መከታ አድርገው ከደረጁ አገሮች በኩል አንዳንድ መገናኛ ብዙኀን፣ ኢትዮጵያ ፣ ለሥነ ፈለክ ምርምር የሰጠችውን ግምት ፣ የቅንጦት አስመስለው ነው የተመለከቱት። የኢትዮጵያ የኅዋ ሳይንስ ድርጅት(Ethiopian Space Science Society) እና የእንጦንጦው የሰማይ አካላት መመልከቻና የኅዋ ጥናት ጣቢያ (Entoto Observatory)፣ የኅዋ ምርምር ፤ ለልማት መሠረታዊና ጠቃሚ ድርሻ ፣ እንዳለው ነው የሚያስረዱት። በቅድሚያ ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪቃ ክፍለ ዓለም በኅዋ ምርምር ረገድ ዋና ማዕከል የመሆን ፍላጎት ያሳደረችበት ምክንያቷ ምን ይሆን?

የእንጦንጦው የሰማይ አካላት መመልከቻና የኅዋ ጥናት ጣቢያ (Entoto Observatory)ዋና ሥራ አስኪያጅ (ዳይሬክተር) «አስትሮፊዚስት» ዶክተር ሰሎሞን በላይ ---

በኅዋ ላይ ያተኮረው ምርምር በዚያው አቅጣጫ የላቀ ዕውቀት ለመግብዬት የሚያስችል ቢሆንም፤ ከሃገሪቱ መሠረታዊ ችግሮችና የዕድገት ተስፋ ጋር በተያያዘ ፤ በአጠቃላei፣ በየብስ ላይ በሚደረግ ምርምር ያለው አስተዋጽዖ እስከምን ድረስ ይሆን---

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic