የቻይና ጠ/ሚኒስትር በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 05.05.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የቻይና ጠ/ሚኒስትር በኢትዮጵያ

የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኬኪያንግ ምጣኔ ሀብታዊ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ወደ አራት የአፍሪቃ ሀገራት ጉዞ ጀምረዋል።

ሊ ጉብኝታቸውንም የጀመሩት ከኢትዮጲያ ነው። ትናንት አዲስ አበባ የገቡት የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኬኪያንግ ከኢትዮጵያ በመቀጠል ወደ ናይጄሪያ፣ አንጎላ እና ኬንያ ይጓዛሉ። አፍሪቃ አንድ ሳምንት የሚቆዩት ሊ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ ወደ አፍሪቃ ሲጓዙ ይህ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ነው። ኢትዮጵያ፤ ቻይናዊው ጠ/ሚኒስትር በመጎብኘት ላይ ካሉት አራት የአፍሪቃ ሀገራት አንዷ ብቻ ሳትሆን የመጀመሪያዋም ናት። አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ «ኤርንስት ኤንድ ያንግ» በተባለው አለም አቀፍ የቢዝነዝ አማካሪ ድርጅት የኢትዮጵያው ቅርንጫፍ ኃላፊ ናቸው። እንደሳቸው ከሆነ የኢትዮጵያ እና የቻይና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ከሌሎች የአፍሪቃ ሀገራት ጋ ሲነፃፀር ጠንካራ እና ሰፊ ነው።

China in Afrika African Union AU

በቻይና መንግሥት ድጋፍ የተሰራው አዱሱ የአፍሪቃ ህብረት አዳራሽ

የአፍሪቃ የንግድ አጋር የነበረችውን ዮናይትድ ስቴትስን ገበያ ከአምስት አመት በፊት ቻይና ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥራዋለች። በአህጉሩ በሚገኙ 2500 የቻይና ኩባኒያዎች ባለፈው አመት የነበረው የንግድ ግንኙነት 210 ቢሊዮን ዶላር እንደሚጠጋ የቻይና ዜና ወኪል ሺንሃ ዘግቧል። ታድያ ቻይና በአፍሪቃ ያላትን ከፍተኛ ተሳትፎ የሚቸቹ እና እንዲያውም ከዘመናዊ ቅኝ ግዛት ጋር የሚያመሳስሉም አልጠፉም። ይሁንና የቻይናው ጠ/ሚኒስትር አፍሪቃውያን አጋሮቻቸው ከቅኝ ግዛት ጋር በተያያዘ ፍጹም ስጋት እንዳያድርባቸው አሳስበዋል። «የኤርንስት ኤንድ ያንግ» የቢዝነዝ አማካሪ ድርጅት የኢትዮጵያው ቅርንጫፍ ኃላፊ አቶ ዘመዴነህ በበኩላቸው ቻይና ከአፍሪቃ በተለይም ከኢትዮጵያ ጋር ባላት ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ጥቅሙ ለኢትዮጵያ እንደሚያመዝን ያምናሉ።

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic