የቻይና ድርጅቶች እና የአፍሪቃውያን ትችት | አፍሪቃ | DW | 04.06.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የቻይና ድርጅቶች እና የአፍሪቃውያን ትችት

አፍሪቃ ውስጥ በቻይናውያን ላይ በርካታ ትችቶች ይሰማሉ። የተፈጭሮ ሀብታችንን ይበዘብዛሉ፣ የስራ ቦታችንን ይሻሙብናል፣ ለሚቀጥሯቸው ሰራተኞች በደንብ አይከፍሉም። ሌላም ሌላም። በርግጥ ይህ እውነት ነውን? ቻይናውያን ለአህጉሯ መጥፎ ይሆኑ?

ቻይናውያን በአፍሪቃ እዚሁ ቦን አቅራቢያ በኮሌኝ ከተማ በተኪያሄደ ስብሰባ ላይ የአፍሪቃ የኢኮኖሚ ተንታኞች ካነሱት ርዕስ አንዱ ነው። ቻይናውያን በአሉታዊ መንገድ ብቻ ሳይሁን በአዎንታዊ ጎንም ሳይነሱ አላለፈም።

ኢስማሌል ምሪሾ ከቻይናውያን ጋ የነበረው ተሞክሮ ጥሩ ነው። ታንዛናዊው ወጣት ላለፉት 7 ዓመታት ነጭ ሽንኩርት ከቻይና በማስገባት ወደ ሌሎች የአፍሪቃ አገሮች ለሚሸጥ አንድ ትንሽ ድርጅት ይሰራል። ምሪሾ አብሯቸው ስለሚሰራ ቻይናውያን ለጓደኞቹ ሲነግር ግን የሚሰማው ወቀሳ ብቻ ነው። የራሳችንን ነጭ ሽንኩርት እንዳንሸጥ ቻይናውያን አቅራቢ ይሆናሉ የመሳሰሉ ወቀሳዎችን ይሰማል። የምሪሾ እይታ ግን ከዚህ ይለያል። የቻይና ነጭ ሽንኩርት ፍሬዎች ከታንዛኒያዎቹ ጋ ሲነፃፀሩ ትላልቅ ናቸው። ስለሆነም ሰው ይመርጣቸዋል። ታንዛናዊያን ይህንን ፍላጎት ማሟላት ላልቻሉ የራሳቸው ጥፋት ነው ባይ ነው።

Titel: Die chinesische Wissenschaftlerin Katy Lam Schlagworte: China, Afrika, Migration, Diskriminierung Wer hat das Bild gemacht?: Adrian Kriesch Wann wurde das Bild gemacht?: 31.5.2012 Wo wurde das Bild aufgenommen?: Tagung der Vereinigung für Afrikawissenschaften in Köln Bildbeschreibung: Bei welcher Gelegenheit / in welcher Situation wurde das Bild aufgenommen? Wer oder was ist auf dem Bild zu sehen? Die chinesische Wissenschaftlerin Katy Lam von der Universität Lausanne in der Schweiz bei der Tagung der Vereinigung für Afrikawissenschaften in Köln In welchem Zusammenhang soll das Bild/sollen die Bilder verwendet werden?: Artikel

ኬቲ ላም

« በርካታ አፍሪቃውያን የቻይናውያን ፀባይን እና የስራ አመራር ይወቅሳሉ። ለኛ ለአፍሪቃውያን ደንታ እና ከበሬታ የላቸውም ይላሉ። እኔ በበኩሌ አለቃዬ በጣም ጥሩ ሰው ነው። አልፎ አልፎ አብረን ወጣ እንላለን። ጥሩ ይከፍለኛል። ሊረዳኝም ይሞክራል። ከሌሎች ግን እውነቱን ለመናገር የምሰማው ተቃራነውን ነው። ቻይናውያን እዚህ የሚመጡት ትርፋማ ለመሆን እና ተመልሰው ወደ አገራቸው መሄድ እንደሚፈልጉ ብቻ ነው።»

ከሲውዘርላንድ ዮንቨርሲቲ የመጡት የኢኮኖሚ ምሁር ኬቲ ላምም ይህንን ነው የሚያረጋግጡት። ጋና እና ቤኒን ውስጥ ባለሙያዋ ለበርካታ ወራት ከቻይናውያን እና የአገሬው ህብረተሰብ ጋ ተወያይተዋል።

«በርካቶች በአፍሪቃ ያሉት ቻይናውያንን የቻይና መንግስት የላካቸው ነው የሚመስላቸው።ነገር ግን ይህ ልክ አይደለም። ከመንግስታቸው ድጋፍ እንኳን አያገኙም። በራሳቸው የሚንቀሳቀሱ ናቸው። ሁኔታው እንደማንኛውም ወደ ሌላ ቦታ የሚሄድ የውጭ አገር ዜጋ ለነሱም ቀላል አይደለም። ብዙ ጊዜ በቋንቋ ችግር የተነሳ ከአገሩ የአኗኗር ስልት ጋ መላመድ የሚያቅታቸው ይመስለኛል።»

በተለይ የቻይና ድርጅቶች አፍሪቃ ውስጥ እክል ይገጥማቸዋል። በነሱ ላይ የሚሰማው ወቀሳ በአንዳንድ የአፍሪቃ አገሮች የፖለቲካ ማራመጃ ሆኗል ይላሉ ካቲ ላም። የምርጫ ዘመቻ ሰሞን የቻይናውያን ጥላቻ የሚገልፁ ድምፆች በአንዳንድ የአፍሪቃ አገሮች መታዘባቸውን ያስረዳሉ። «በቤኒን 40 የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች ነበሩ አሁን ግን ሶስት ብቻ ናቸው የቀሩት፤ ሌሎቹ ፍቃዳቸውን ተነጥቀዋል» ይላሉ ላም። እንደ ሎሬንስ ማርፌኒግ አመለካከት አትራፊዎቹ ቻይናውያን ብቻ ሳይሆኑ አፍሪቃውያንም ናቸው። ማርፌኒግ ጀርመን የሚገኝ GIGA የተሰኘ የጥናት ተቋም ሰራተኛ ናቸው። በሴኔጋል እና ጋና ከትናንሽ ቻይናውያን ነጋዴዎች ጋ ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ይሞክራሉ። ቻይናውያን የጎዳና ተዳዳሪዎችን ቀጥረው በማሰራት በርካታ አፍሪቃውያን ወደ አውሮፓ እንዳይሰደዱ እድል ሰቷል ሲሉ ይገልፃሉ።

« ከጥቂት አመታት በፊት ለስደት የተዘጋጁ እጩዎች ነበሩ። ለእነሱ ከቻይናውያን ጋ ተባብረው በመስራት እድል ተከፍቶላቸዋል።አገር ጥለው ሳይሰደዱ በዚህ አጋጣሚ ገንዘብ ለማፍራት እና ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት ችለዋል። ዳካር ወይንም ጋና ውስጥ ስለ ቻይናውያን ወቀሳ ከተሰማ በብዛት ነጋዴዎች ናቸው። ግን አዎ ቻይናውያን ስራ ይሰጡናል ገንዘብ ለማፍራትም እድል ይከፍቱልናል። »

በአፍሪቃ ያሉ የቻይናውያን ገፅታ በተናጥል መመልከት እንደሚገባ የኢኮኖሚ ምሁሮቹ ይስማማሉ። በርግጥ መጥፎ ነገሮች ሲከሰቱም ይታያል። ከቻይና በሚገቡ ርካሽ ጫማዎች ሽያጭ የተነሳ ሴኔጋል ውስጥ 17 የተዘጉ የጫማ ፋብሪካዎች ማርፌኒግ ቆጥረዋል። ይሁንና እንደ ኢስማሌል ምሪሾ ያሉ አትራፊዎች እንዳሉም ልንዘነጋ አይገባም ሱሉ ያሳስባሉ።

አድሪያን ክሪሽ

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic