የቻይና እና የአፍሪቃ ግንኙነት
ቅዳሜ፣ ሐምሌ 14 2004ማስታወቂያ
አዲሱ ብድር መሠረተ ልማቱን ለማሻሻል፡ የግብርናውንና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለማሳደግ እና ለትናንሾቹ እና ለመካከለኞቹ የንግድ ዘርፎች እንደሚውል ፕሬዚደንቱ አስረድተዋል። የአውሮጳ ህብረት ቻይና በሰብዓዊ መብት ይዞታቸው ለሚወቀሱ እና መልካም አስተዳደር ለጎደላቸው አፍሪቃውያት ሀገራት ብድር የምትሰጥበትን አሰራር ይወቅሳል። አፍሪቃውያን እአአ በ 1950 ዓመታት ያካሄዱትን ፀረ ቅኝ አገዛዝ ትግል የደገፈችው ቻይና በወቅቱ ዋነኛዋ የአፍሪቃ የንግድ አጋር ናት። በቻይናውያን መዘርዝሮች መሠረት የንግዱ መጠን ወደ 166 ቢልየን ዶላር ይደርሳል።
አርያም ተክሌ
መሥፍን መኮንን