የቻይና ኤኮኖሚ | ኤኮኖሚ | DW | 05.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኤኮኖሚ

የቻይና ኤኮኖሚ

የቻይና ኤኮኖሚ ባለፉት ሁለት አሠርተ ዓመታት ባለሁለት አሀዝ እድገት በማስመዝገብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሁለተኛዋ ናት። ይኸው 12,2% የነበረው የእድገት መጠን ግን በሚቀጥሉት ጊዚያት በጉልህ ሊቀንስ እንደሚችል የምጣኔ ሀብት ጠበብት ገምተዋል። ይህም በቻይና ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ በዓለም ኤኮኖሚ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳርፍ እንደሚችል ጠበብት ጠቁመዋል።

ቻይና እአአ በ2015 ዓም ከ6,9 እስከ 7,1% የኤኮኖሚ እድገት ልታስመዘግብ እንደምትችል የሀገሪቱ መንግሥት በይፋ ያወጣው ትንበያ አስታውቋል። ይኸው ትንበያ በመጀመሪያ ሲመለከቱት እና ደከም ያለ የኤኮኖሚ እድገት ካሳዩት ምዕራባውያት ሀገራት ኤኮኖሚ ጋ ሲያነፃፅሩት በጣም አስገራሚ ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም፣ ፈጥነው በማደግ ላይ የሚገኙ ቻይናን የመሳሰሉ በመልማት ላይ ያሉ ሀገራት በቂ የስራ ቦታ ለመፍጠር እና ማህበራዊ ሰላምን ለመጠበቅ ሲሉ ከአደጉት ጀርመንን ከመሳሰሉ ሀገራት ይበልጥ በከፍተኛ እድገት ላይ ጥገኛ ናቸው። እና እድገቱ ከ12,2% በቀጣዩ ጊዜ ወደ ወደ ስድስት እና ሰባት ከመቶ ይቀንሳል መባሉ በመረጋጋቷ ላይ ስጋት ሊደቅን እንደሚችል ተንታኞች ይገምታሉ። ለዝቅተኛ እድገት ራሱን ያዘጋጀው የቻይና መንግሥት በቁጠባ፣ በኢንቬስትመንት እና በውጭ ንግድ ላይ አትኩሮ የነበረው የኤኮኖሚ ፖሊሲው በዘላቂነት ሊቀጥል እንደማይችል በመረዳት፣ አሁን የሀገር ፍጆታን ለማሳደግ ዕቅድ አለው። ይህ ግን ተቃውሞ ሊገጥመው እና ጊዜም ሊወስድ እንደሚችል የምጣኔ ሀብት ጠቢብ አሜሪካዊው ኑርየል ሩቢኒ አስታውቀዋል።

« ፕሬዚደንት ዢ ጂንፒንግ በመጀመሪያ ፖለቲካዊ ሥልጣናቸውን ማጠናከር ይፈልጋሉ። ከእድገቱ ጥቅም ያገኙ በነበሩት በመንግሥት በተያዙ ተቋማት፣ ባካባቢ መንግሥታት፣ በብሔራዊው ነፃ አውጪ ጦር እና በመንግሥት ዘርፎች አንፃር እየተከተሉ ነው። ስለዚህ ሥልጣናቸውን ካጠናከርሩ እና በሥልጣናቸው ከተማመኑ፣ ምናልባት ያኔ አንዳንዶቹ የተሀድሶ ዕቅዶቻቸው ሊጀመሩ ይችሉ ይሆናል። »

በርግጥም፣ ይደረጋሉ የሚባሉት ብዙዎቹ ተሀድሶዎች ከብዙ ጊዜ ጀምረው ተግባራዊ የሚሆኑበትን ጊዜ በመጠባበቅ ላይ ናቸው፣ የሀገር ውስጥ ፍጆታን እና ኤኮኖሚዋን እሴት ለማሳደግ የያዘችውን ዕቅድ ጀርመናውያን አሞግሰዋል። እአአ በ2013 በቻይና ጠቅላላ ብሔራዊ ምርት መካከል ኢንቬስትመን 50%፣ የግል ፍጆታ 35% ሲሸፍን፣ በጀርመን ኢንቬስትመንት ከጠቅላላ ብሔራዊ ምርት መካከል 17%፣ የግል ፍጆታ ደግሞ ስድሳ ከመቶ ይጠጋ ነበር።

የቻይና ኤኮኖሚ እድገት የግሉን ፍጆት ለማሳደግ እና ኢንቬስትመንትን ለመቀነስ ሲባል የሚደረገው የደሞዝ ጭማሪ የኤኮኖሚውን እድገት ሊቀንሰው የሚችልበት ስጋት መኖሩን ነው ጠበብት ያመለከቱት፣ የጀርመን ባንክ የእስያና ፓሲፊክ አካባቢ ተጠሪ ሚሻኤል ስፔንሰር እንዳስረዱትም፣ በንብረት ገበያ ላይ የሚፈሰው ወረት በሀገሪቱ ኤኮኖሚ እድገት ላይ ተፅዕኖ ማሳረፉ አይቀርም።

« በቻይና የኤኮኖሚውን እድገት ወደኋላ የጎተተው የቀዘቀዘው የቤት ግንባታ ገበያ ሂደት ነው። አጠቃላዩ የኤኮኖሚ ሁኔታ ካለፈው መስከረም ወዲህ ቢሻሻልም፣ ለቤት ግንባታው ዘርፍ የፈሰሰው ወረት እየቀነሰ ነው የመጣው። የመንግሥቱ ወጪም ዝቅ እያለ መሄዱ አይቀርም፣ ይህም በሀገር ውስጥ እድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳርፋል። ይህንን ለማስተካከል መንግሥት በተያዘው የአውሮጳውያኑ መጋቢት እና በቀጣዩ ግንቦት ወር አንዳንድ የቀረጥ ቅነሳ ያደርጋል። »

ቶማስ ኮልማን/አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic