የትግራይ ክልል ም/ር አስተያየትና እንደምታዉ | ኢትዮጵያ | DW | 19.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የትግራይ ክልል ም/ር አስተያየትና እንደምታዉ

ሰሞኑን የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ያደረጉት ንግግር በፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን ትችት እየቀረበበት ነው፡፡ ዶክተር ደብረፅዮን ሰሞኑን ለመንግስታዊው ትግራይ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ ምልልስ ወቅቱ የደርግ ባለስልጣናት የነበሩና ሌሎች ሐይሎች በህዝብ ላይ ጫና ለመፍጠር እየሰሩ ያሉበት ነው ብለዋል፡፡ 

ሰሞኑን የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ያደረጉት ንግግር በፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን ትችት እየቀረበበት ነው፡፡ ዶክተር ደብረፅዮን የኢትዮጵያ ፌደራላዊና ሕገ መንግስታዊ ስርዓት አደጋ ላይ የሚጥሉ ተግባራት መንግስታቸው በዝምታ እንደማይመለከተው ሲገልፁ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ አቶ ቻላቸው ታረቀኝ የፌዴራል ስርዓቱ አደጋ ላይ መውደቅ ከአንድ የፖለቲካ ኃይል ብቻ የሚሰማ አስተያየት ነው ብለዋል፡፡ ዶክተር ደብረፅዮን ሰሞኑን ለመንግስታዊው ትግራይ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ ምልልስ ወቅቱ የደርግ ባለስልጣናት የነበሩና ሌሎች ሐይሎች በህዝብ ላይ ጫና ለመፍጠር እየሰሩ ያሉበት ነው ብለዋል፡፡ የፌደራልና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱ አደጋ ላይ እየወደቀ ነው ያሉት የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር መንግስታቸው ጉዳዩ በቸልታ እንደማይመለከተው በመግለፅ " እርምጃ እንወስዳለን" ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት የሰጡን በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ አቶ ቻላቸው ታረቀኝ ውጭ የነበሩ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች ወደ ሀገር መግባታቸው ለውጡ የፈጠረው አወንታዊ እርምጃ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የፌደራል ስርዓቱ መሸራረፍ፣ ሕገ መንግስቱ መጣስ በተደጋጋሚ በአንድ የፖለቲካ ሐይል ብቻ እየተነሳ ነው ያለት ምሁሩ በሚባለው መጠን ስጋት የለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

 

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 

አዜብ ታደሰ 

ሸዋዬ ለገሠ 

Audios and videos on the topic