1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር መግለጫ

ሰኞ፣ ኅዳር 10 2011

በሰብአዊ መብት ጥሰትና ሙስና ተግባራት በተጠረጠሩ አካላት እየተወሰደ ያለው እርምጃ፣ ሂደቱ፣ ከሕጋዊነት ይልቅ ፖለቲካዊ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም ሲሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ፡፡ ም/ርእሰ መስተዳድሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፣ በሂደቱ የውጭ ኃይል ጣልቃ ገብነት አለበት።

https://p.dw.com/p/38XQV
Äthiopien Debretsion Gebremichael
ምስል DW/M. Haileselassie

ሂደቱ የውጭ ኃይል ጣልቃ ገብነት አለበት

ጉዳዩም የሕግ የበላይነት ማስከበር ላይ ሳይሆን ለሌላ የፖለቲካ አጀንዳ መጠቀሚያ እንዳይሆን ስጋታቸውን የገለጹት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን በሂደቱ ስጋታቸውን የሚያሳዩ ክፍተቶች እየተስተዋሉ ነው፣ "በትግራይ ህዝብ ላይ ጫና ለመፍጠር በተደጋጋሚ ሙከራ ሲደረግ ቆይቷል፣ አሁን ደግሞ በሌላ መንገድ ተመልሶ እንደ አዲስ መጥቷልም" ብለዋል፡፡

ሚልዮን ኃይለ ሥላሴ

አርያም ተክሌ

ማንተጋፍቶት ስለሺ