የትንሳኤ ዕለት ተቃዉሞ ሰልፍ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 01.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የትንሳኤ ዕለት ተቃዉሞ ሰልፍ

ጀርመን ሀገር በጎርጎሮሳዊዉ የዘመን ቀመር የትንሳኤ በዓል በሚከበርበት ወቅት የተቃዉሞ ሰልፍ ማካሄድ ከተለመደ ዉሎ አድሯል።

 ሲቪሉ ኅብረተሰብ በብዛት የሚሳተፍበትና ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የሚያነሳዉ የትንሳኤ ዕለት ተቃዉሞ ሰልፍ ዘንድሮም ከዕለተ ዓርብ ማለትም የስቅለት ቀን አንስቶ እስከትንሳኤ ማግስት ማለት ማዕዶት ቀን ድረስ ኅብረተሰቡን የሚያሳስቡ ጉዳዮች ተነስተዉ ለፖለቲከኞች መልዕክት ይተላለፋል። በዘንድሮዉ የትንሳኤ በዓላቸዉ ጀርመኖች አራት አበይት ያሏቸዉን ጉዳዮች አንስተዉ ከዓርብ ዕለት ጀምረዉ በተለያዩ ከተሞች ተቃዉሞ አሰምተዋል። የተቃዉሞ ሰልፉ ህዝብ በብዛት በሚንቀሳቀስባቸዉ አካባቢዎች በተለያዩ ሁኔታዎች የሚከናወን እንደመሆኑ የተነሱ ነጥቦችን እንዲያጋራን የበርሊን ወኪላችንን ይልማ ኃይለሚካኤልን በስልክ አነጋግሬዋለሁ፤

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic