የትንሳኤ በዓል ተከበረ | ኢትዮጵያ | DW | 02.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የትንሳኤ በዓል ተከበረ

የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዉያን ዛሬ የእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓልን በድምቀት አከበሩ። ክብረ በዓሉን አስመልክቶ የሐይማኖት አባቶች «መልካም ተግባር በመፈፀም ማክበር እንደሚገባ» መናገራቸዉ ተመልክቶአል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባስተላለፉት መልእክት፥ ምዕመናን ከሐይማኖቱ የተወረሱ እሴቶችንና ባህሎችን በጠበቀ መልኩ በዓሉን ሊያከብሩ እንደሚገባ መናገራቸዉም ታዉቋአል። ፓትርያርኩ በዓሉን በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን፣ በጋምቤላ ክልል ግድያና የአፈና የደረሰባቸዉቸው በኃዘንና በችግር ላይ ከሚገኙ ወገኖች ጎን በመሆን እንዲሁም አረጋውያንንና አሳዳጊ የሌላቸውን ሕጻናት በማሰብ ሊከበር እንደሚገባ መናገራቸዉ ታዉቋል።

ኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብጹዕ ካርዲናል አቡነ ብርኃነ ኢየሱስ በበኩላቸው፥ በዓሉን ስናከብር ችግረኞችንና አቅመ ደካሞችን በማሰብ መሆን ይገባል ማለታቸዉ ተዘግቦአል። መዲና አዲስ አበባ ላይ የበዓሉ አከባበር እንዲት እንደነበር የአዲስ አበባዉ ወኪላችንን ጠይቀነዉ ነበር።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic