የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ዓመታዊ ዘገባ | ዓለም | DW | 12.07.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ዓመታዊ ዘገባ

በየሃገሩ ሙስና የሚገኝበትን ደረጃ የሚገመግመው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ዘንድሮ በትላልቅ ኩባንያዎች ደረጃ ሙስና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የመረመረበትን ዘገባ አቅርቧል ። በዚሁ ምርመራ ተቋሙ ግዙፍ ድንበር ዘለል ኩባንያዎች ሙስናን ለመከላከል

Transparency International Logo

በየሃገሩ ሙስና የሚገኝበትን ደረጃ የሚገመግመው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ዘንድሮ በትላልቅ ኩባንያዎች ደረጃ ሙስና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የመረመረበትን ዘገባ አቅርቧል ። በዚሁ ምርመራ ተቋሙ ግዙፍ ድንበር ዘለል ኩባንያዎች ሙስናን ለመከላከል ስለ ሚወስዷቸው እርምጃዎች ና የገንዘብ ዝውውራቸው ምን ያህል ግልፅ አሰራርን እንደሚከተል ጥናት አካሂዷል ። የዶቼቬለው ማቲያስ ቦሊንገር የጥናቱ ውጤት ላይ ያተኮረ ዘገባ አሰናድቷል ። ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ።

ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ሙስና በየሃገሩ የሚገኝበት ደረጃ ላይ ማትኮሩን ትቶ በኩባንያዎች ምን ዓይነት ባህርይ እንዳለው ዝርዝር ጥናት ሲያቀርብ የዘንድሮው የመጀመሪያው ነው ። ጥናቱም ነው ጥናት በ200 አገሮች ውስጥ በሚሰሩ 105 ድንበር ዘለል ኩባንያዎች ላይ ነበር ያተኮረው ። የትርንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የጀርመን ቅርንጫፍ ሊቀመንበር ኤዳ ሙለር እንደሚሉት በተለይ በድሃዎቹ አገሮች አሰራሩ ግልፅነት ይጎድለዋል ።

Eine Hand reicht am Dienstag (18.10.2005) in Schwerin einen Umschlag mit Bargeld über einen Schreibtisch. (Illustration zum Thema Vorstellung des Korruptionswahrnehmungsindex vom 18.10.2005) Transparency International (TI) stellt am selben Tag in Berlin und London seinen jährlichen Korruptionsbericht vor, in dem über 150 Staaten klassifiziert werden. Deutschland rutschte in dem Bericht vom 15. auf den 16. Platz, erzielte aber wie im Vorjahr 8,2 von 10,0 möglichen Punkten. Auf dem letzten Platz des Index rangieren Bangladesh und der Tschad. Foto: Jens Büttner/lmv (zu dpa 4088 vom 18.10.2005) +++(c) dpa - Bildfunk+++

« እነዚህ ኩባንያዎች ንግድ በሚያካሂዱባቸው አገሮች ስለሚያገኙትኝ ትርፍና ስለ ሚከፍሉት ቀረጥ በግልጽ የሚታወቀው በአማካይ ጥቂት ነው ። ይህ የሚከሰተውም ብዙውን ጊዜ እጅግ በደኽዩና አጠያያቂ መንግሥታዊ መዋቅር ባላቸው ሃገራት ነው »

ፎርብስ በተባለው የአሜሪካን መፅሄት ላይ የተዘረሩ 105 በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኩባንያዎች ፣ በንግድ ያገኙትን ገቢ ና የሚከፍሉትን ቀረጥ በግልፅ ያሳውቁ እንደሆነና ምን ዓይነት የሙስና መከላከያ መርሃ ግብር እንዳላቸው ነበር ጥናቱ የገመገመው ። መረጃዎቹ የተሰበሰቡትም የኩባንያዎቹን ድረ ገጾች ከመሳሰሉ ምንጮች ነው ። በግምገማው መሰረት የኖርዌዩ የነዳጅ ዘይት ኩባንያ Statoil ና የብሪታኒያና የአውስትሬሊያው ማዕድን አውጭ ኩባንያ ሪዮ ቲንቶ አንድኛ እና ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል ።የቻይናውያኑ ባንክ ኦፍ ኮምዩኒኬሽን ና የቻይና ባንክ የመጨረሻ ደረጃ ነው የተሰጣቸው ።ሮቢን ሁድስ የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የጥናት ክፍል ባልደረባ ምክንያቱን ያስረዳሉ ።

Berlin/ ARCHIV: Die Vorsitzende von Transparency International Deutschland, Edda Mueller, posiert in Berlin mit dem Nationalen Integritaetsbericht Deutschland des Vereins (Foto vom 19.01.12). Transparency International aeussert sich am Dienstag (09.07.12) in Berlin zur Vorstellung des Berichts zu Antikorruptionsmassnahmen. (zu dapd-Text) Foto: Sebastian Willnow/dapd

ኤዳ ሙለር

« ያየነው ምንድን ነው በመዘርዝሩ ጠርዝ ላይ ያሉት ቻይናን የመሳሰሉ አገሮች የዓለም ዓቀፍ ደንብና ደረጃን አሟልተው ለመገኘት በአዲስ መልክ ሥራቸውን ማካሄድ አለባቸው ። ግን ደንቦቹ በአፋጣኝ ይለዋወጣሉ ። ባለፈው ዓመት ቻይና በተለይ ችግሩን በውጭ አገር ለመከላከል ፀረ ሙስና ህግ አውጥታለች ። ይህም ከ ከኤኮኖሚ ትብብርና ልማት ድርጅት ፀረ ሙስና ህግ ጋር እንዲጣጣም አድርጋ ነበር ። ስለዚህ በነዚህ ኩባንያዎች ላይ ጫና በማድረግ ሙስናን ለመታገል ዓለም ዓቀፉን ግፊት ማጠናከር ጠቃሚ ነው ።

የአዳዲሶቹ ቴክኖሎጂዎች ባለቤቶች እንደ ጉግል አፕል ና አማዞን የመሳሰሉትም ደካማ ሆነው ነው የተገኙት ። እነዚህ ኩባንያዎች በመዘርዝሩ ከመጨረሻዎቹ 5 ኩባንያዎች በላይ ደረጃ ነው ያገኙት ። በፋይናንሱ ዘርፍ የሚገኙ ኩባንያዎችም የተሻለ ደረጃ ላይ አልተገኙም ። ግዙፎቹ የገንዘብ ተቋማት ጎልድማን ሣክስ ፣ ባንክ ኦፍ አሜሪካ እንዲሁም ቪዛና ሲቲ ግሩፕ በመዘርዝሩ ከመጨረሻዎቹ 3 ኩባንያዎች በፊት ያሉትን ቦታዎች ነው የያዙት ደረጃ ላይ ናቸው ። እንደገና ሙለር

Übergabe von 100-Euro-Banknoten (Illustration zum Thema Korruption), aufgenommen am Montag (06.11.2006) in Berlin. Die Anti-Korruptions-Organisation Transparency International (TI) stellte den Korruptionsindex 2006 vor. Deutschland zählt nach Angaben von TI weltweit zu den 20 Ländern mit der geringsten Korruption. Foto: Gero Breloer +++(c) dpa - Report+++

« እንደኛ አመለካከት ጥናቱ ያሳየው በተለይ ለፋይናንሱ ዘርፍ ተጨማሪ ደንቦችና አሰገዳጅ የሆነ መደበኛ ዘገባዎች ማቅረብ አስፈላጊ ነው ። ባናኮች የሚሳተፉበትን መመሪያ ና የገንዘብ ድርሻቸውን በግልፅ ማሳየት አለባቸው ። የመታደጊያ ገንዘብ ከቀረጥ ከፋዩ ወስዶ በያንዳንዱ ሃገር በአግባቡ ቀረጥ መከፈሉን ማረጋገጥ የሚያስችለውን ሰነድ በይፋ ለማቅረብ ፈቃደኛ አለመሆን የሚያስኬድ አይደለም ። »

በጥናቱ ከተካተቱት 7 የጀርመን ኩባንያዎች ውስጥ ሶፍትዌር አምራቹ SAP የኬሚካል ኩባንያው BASF ና የመድን ዋስትናው ኩባንያ Allianz ጥር ደረጃ አግኝተዋል ። ሰባቱ የጀርመን ኩባንያዎች በደረጃው ሰንጠረዥ ከአንደኛ ሶስተኛዎቹ በላይ ነው የተቀመጡት ። ይሁንና ኤዳ ሙለር የጀርመን ጥሬ አላባ አምራች ኩባንያዎች በአውሮፓ በተደነገገው ህግ መሰረት ገቢና ወጪያቸውን በግልፅ እንዲያሳውቁ ባለማድረግ የፌደራል ጀርመን መንግሥትን ተችተዋል ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 12.07.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15VxL
 • ቀን 12.07.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15VxL