የትራምፕ ዉሳኔ እና የበካይ ጋዞች ቅነሳ | ጤና እና አካባቢ | DW | 06.06.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

የትራምፕ ዉሳኔ እና የበካይ ጋዞች ቅነሳ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እንደተገመተዉ ሀገራቸዉ ከባቢ አየር በካይ ጋዞችን ለመቀነስ ሃገራት ከተስማሙበት የፓሪሱ የአየር ንብረት ስምምነት እንደምትወጣ አሳዉቀዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 11:15

የትራምፕን ዉሳኔ የአሜሪካን ዜጎችም ተቃዉመዉታል፤

ለዓለማችን ከባቢ አየር ብክለት በግንባር ቀደምትነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉት አንዷ የሆነችዉ ዩናይትድ ስቴትስ ከዚህ ዉል መዉጣቷን ይፋ ብታደርግም ሌሎች በርካታ ሃገራት ግን በዉላቸዉ እንደሚፀኑ እየገለጹ ነዉ። ዋሽንግተን በጎርጎሪዮሳዊዉ 1997 ዓ,ም ከተፈረመዉ ከታሪካዊዉ የኪዮቶ ስምምነት አንስቶ የአየር ንብረት ለዉጥን ለመግታት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ዉስጥ ከቀሪዉ የዓለም ሃገራት ጋር ተባብራ ላለመሳተፍ ምክንያቶችን እየደረደረች ራሷን ስታገልል ታይቷል። 84 ሃገራት የኪዮቶን ዉል ፈርመዋል። አስገዳጅ የነበረዉ የኪዮቶ ዉል የጊዜ ገደቡ ሲያበቃ የሙቀት አማቂ ጋዞችን ልቀት በመቆጣጠር የአየር ንብረት ለዉጥን ለመግታት ይረዳል ተብሎ የታሰበዉን

የፓሪስ ስምምነት የተቀበለችዉ ዩናይትድ ስቴትስ በአዲሱ ፕሬዝደንቷ «የአየር ንብረት ለዉጥ የሚል ነገር የለም» በሚል አቋም ምክንያት ዳግም ከሌላዉ ዓለም የተለየ መንገድ ጀምራለች።  የዋሽንግተን ዉሳኔ  ምን ያስከትላል፤ ተግባራዊነቱስ እንዴት ነዉ? የዩናይትድ ስቴትስ ብዙ ከተደከመለት የፓርስ የአየር ንብረት ስምምነት መዉጣት እንደኢትዮጵያ ላሉ ሃገራት ምን ማለት ይሆን? የሚሉትንና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎች በማስናት በካናዳ ካልጋሪ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ተፈጥሮ ዲዛይን ፋኩልቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር እና የዘርፉ ተመራማሪ፤ ለሆኑት ዶክተር ጌታቸዉ አሰፋ፤ እንዲሁም በኢትዮጵያ የደንና የአካባቢ ጥበቃ ሚንስቴር የአየር ንብረት ለዉጥ ትግበራ ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ደባሱ ባይየለኝን አነጋግረናል። የመጀመሪያዉን ክፍል ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic