የትራምፕ ዉሳኔ እና የሌሎች አቋም | ዓለም | DW | 09.05.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የትራምፕ ዉሳኔ እና የሌሎች አቋም

የተቀረዉ ዓለም ዉሳኔዉ ዲፕሎማሲያዊ ድርድርን ዋጋ የሚያሳጣ፤ ዓለም አቀፍ ሠላምን የሚያወክ በማለት ቅሬታዉን እየገለጠ ነዉ።ሥምምነቱን የፈረሙት ራስዋ ኢራን፤ ሩሲያ፤ ቻይና፤ ብሪታንያ፤ ፈረንሳይ፤ ጀርመን እና የአዉሮጳ ሕብረት ዉሉ እንደማይፈርስ አስታዉቀዋል

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:00

በፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት የፀደቀ ሥምምነት ነዉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራንን የኑክሌር መርሐ-ግብር ያስቆመዉን ሥምምነት ማፍረሳቸዉን ከሁለት ሐገራት በስተቀር መላዉ ዓለም ተቃወመዉ። የትራምፕን እርምጃ የደገፉት እስራኤል እና ሳዑዲ አረቢያ ብቻ ናቸዉ። የተቀረዉ ዓለም ዉሳኔዉ ዲፕሎማሲያዊ ድርድርን ዋጋ የሚያሳጣ፤ ዓለም አቀፍ ሠላምን የሚያወክ በማለት ቅሬታዉን እየገለጠ ነዉ። ሥምምነቱን የፈረሙት ራስዋ ኢራን፤ ሩሲያ፤ ቻይና፤ ብሪታንያ፤ ፈረንሳይ፤ ጀርመን እና የአዉሮጳ ሕብረት ዉሉ እንደማይፈርስ አስታዉቀዋል። እንደ ጎርጎርያኑ አቆጣጠር በ2015 የተፈረመዉ ሥምምነት በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት የፀደቀዉ ዉል ነዉ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል። 

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች