የትራምፕ እና ኪም ውይይት ያለ ውጤት መቋጨቱ | ዓለም | DW | 28.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የትራምፕ እና ኪም ውይይት ያለ ውጤት መቋጨቱ

ቬየትናም ሃኖይ ከተማ ትናንት ለሁለተኛ ጊዜ ለመነጋገር የተገናኙት የዩናይትድ ስቴትስ እና ሰሜን ኮርያ መሪዎች ስብሰባ ያለ ውጤት ድንገት መቋረጡ እየተነገረ ነው። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና ፕሬዝደንት ኪም ዮንግ ዑን የአሜሪካን ማዕቀብ አስመልክቶ ያላቸውን አቋም ማለዘብ ባለመቻላቸው የኒኩሊየር ስጋትን ለማስቆም የታለመለት ስብሰባቸው ተቋርጧል።

በቬየትናሟ ሃኖይ ከተማ ትናንት ለሁለተኛ ጊዜ ለመነጋገር የተገናኙት የዩናይትድ ስቴትስ እና ሰሜን ኮርያ መሪዎች ስብሰባ ያለ ውጤት ድንገት መቋረጡ እየተነገረ ነው። አሶሲየትድ ፕረስ እንደዘገበው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና ፕሬዝደንት ኪም ዮንግ ዑን የአሜሪካን ማዕቀብ አስመልክቶ ያላቸውን አቋም ማለዘብ ባለመቻላቸው የኒኩሊየር ስጋትን ለማስቆም የታለመለት ስብሰባቸው ተቋርጧል። ትራምፕ ሰሜን ኮርያ የኒኩሊየር መሣሪያዋን ለማጥፋት ቁጠኝነት ሳታሳይ በዋሽንግተን የተጣለባት ማዕቀብ እንዲነሳ ግፊት ማድረጓን ለንግግራቸው ድንገት መቋረጥ በምክንያትነት ማቅረባቸውንም አክሎ አመልክቷል። የውይይታቸውን ድንገት መቋረጥ አስመልክተው መግለጫ የሰጡት ትራምፕ ያም ቢሆን ሰሜን ኮርያ የሮኬት ፍተሻ ማድረጓን ታቆማለች የሚል ቃል ከኪም ጆን ዑን ማግኘታቸውን ጠቁመዋል።
«ይህም ቢሆን ዋናው ነገር ሊቀመንበር ኪም ትናንት ማታ የሮኬቶች እና ኒኩሊየር ሙከራ እንደማያደርጉ ቃል ገብተዋል። ስለዚህ እኔም አምናቸዋለሁ እናም ቃላቸውን ተቀብያለሁ። ይህም እውነት ነው ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ሆኖም ግን በመካከሉም እንነጋገራለን። ምክንያቱም ይህ የሚቀጥል ሂደት ነው። ነገር ግን ዛሬ መፈራረሙ ተገቢ ነው ብለን አላሰብንም። »
እንዲያም ሆኖ በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረገው ንግግር ድንገት መቋረጡ እጅግም እንዳልገረማቸው አስተያየት የሚሰጡ ጥቂት አይደሉም። 

 

ሸዋዬ ለገሰ

አዜብ ታደሰ