የትምህርት ማስረጃዎች ፍተሻ እና እስር | ኢትዮጵያ | DW | 06.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የትምህርት ማስረጃዎች ፍተሻ እና እስር

ኢትዮጵያ ዉስጥ የትምህርት መረጃን ትክክለኝነት የማጣራት ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ለራዲዮ ጣቢያችን ዶቼ ቬለ ከአድማጮች የተላከ ጥቆማ ያመለክታል። እንዲህ ባለዉ የትምህርት  ማስረጃ የማጣራት ሂደትም በርከት ያሉ የመንግሥት ተቀጣሪዎች የያዙት ማስረጃ ጥያቄ ላይ መዉደቁ ተሰምቷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:56

«ፍተሻዉ መንግሥት የገባዉን ቃል መሠረት ያደረገ ነዉ »

 በተለይ ከደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ የደረሰን ጥቆማ ከ20 የሚበልጡ በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሚያገለግሉ ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃችሁ ሕጋዊ  አይደለም በሚል ለቀናት ታስረዉ በዋስ መለቀቃቸዉን አጣርተናል።

14 እንደሚሆኑ የገለጹልን የተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተቀጣሪዎች ከሚኖሩበት አካባቢ የትምህርት ማስረጃቸዉ ትክክለኛነትን እንዲያረጋግጥላቸዉ ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸዉን ገልጸዉልናል።  መንግሥት የ አሰራር መዋቅሩን ለማሻሻል በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሚሠሩ ተቀጣሪዎች የትምህርት ማስረጃ እዉነተኝነቱን እንዲጣራ በሀገር አቀፍ እና በክልል ደረጃ በተሰጠ መመሪያ መሠረት በሚካሄደዉ ፍተሻ ያለ አግባብ ለእስር መዳረጋቸዉንም ይናገራሉ። ታሳሪዎቹ በማዘጋጃ ቤት በሲቪል ሰርቪስ፤ በሴቶች ጉዳይ በዉኃ ጽህፈት ቤት እና በመሳሰሉት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተቀጣሪዎች ናቸዉ። እያንዳንዳቸዉ ከአምስት ቀን በላይ ታስረዉ በ10 ሺህ ብር ዋስ ተለቀዉ የትምህርት ማስረጃቸዉ ትክክለኛነት ያረጋግጥላቸዉ ዘንድ ከሚኖሩበት አካባቢ አዲስ አበባ ወደሚገኘዉ ሚችከን ኮሌጅ ሄደዋል። እነሱ እንደሚሉት ትምህርታቸዉን  በርቀት በአግባቡ ተከታትለዉ የተመረቁ ቢሆንም የትምህርት ማስረጃቸዉን እዉነተኝነት የሚያጣራዉ መንግሥታዊ አካል በኢንተርኔት ዉስጥ ማለትም ኦንላይን ሊያገኘዉ ባለመቻሉ ፌክ ወይም የሐሰት የትምህርት ማስረጃ እንዳቀረቡ ተደርገዉ ነዉ ከያሉበት ታድነዉ የታሠሩት።

Karte Äthiopien englisch

በወረዳቸዉ ይህን የማጣራት ኃላፊነት ከሲቪል ሰርቪስ፤ ከአቃቤ ሕግ እና ከፖሊስ የተዉጣጡ ሦስት ሰዎች ያሉበት ኮሚቴ መሰየሙንም ገልጸዉልናል። ሁኔታዉን እንዲያብራሩልን ወደ ወግዲ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ወደ አቶ እንዲሪስ ይማም ደወልን።

የታሠሩት ሠራተኞች 21 ወይም 22 እንደሚሆኑ መረጃቸዉ እስኪጣራ ለጊዜው መታሠራቸዉንም አቶ እንዲሪስ አረጋግጠዋል። እንዲያም ሆኖ ሰዎቹ እንደተማሩባቸዉ ከጠቀሷቸዉ ኮሌጆች የማጣራት ርምጃ እንዳልተወሰደ ነዉ የተናገሩት። የትምህርት ማስረጃዉን የማጣራቱ ሂደትም እንደቀጠለ ይናገራሉ። በትምህርት ማስረጃቸዉ ላይ በቀረበ ጥርጣሬ መታሠራቸዉን የገለጹልንን የመንግሥት ሠራተኞች ከርቀት ያስተማረዉ ሚሽከን ኮሌጅ መሆኑን ያረጋገጡልን ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ግዛቸዉ አመራ የመታሠራቸዉ ምክንያት ለእኛም አልገባንም ይላሉ። ሙሉ ቅንሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ  ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች