1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታጋች ተማሪ ቤተሰቦች ጭንቀት

ሰኞ፣ ሐምሌ 1 2016

ባለፈው ሳምንት እረቡ ጠዋት ከአማራ ክልል ተነስተው ወደ አዲስ አበባ ስጓዙ የነበሩ ቁጥራቸው ከ 100 በላይ ይሆናል የተባሉ ተማሪዎች ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ አካባቢ በታጣቂዎች ከታገቱ በኋላ የተማሪዎቹ ቤሰተቦች በጭንቀት ላይ ወድቀዋል፡፡ ከእገታው ሁለት ቀናት በኋላ ከአጋቾች ገንዘብ መጠየቃቸውን ቤተሰቦች ገልፀዋል።

https://p.dw.com/p/4i0yE
ፎቶ ማህደር፤ የአባይ ድልድይ
ፎቶ ማህደር፤ የአባይ ድልድይ ምስል Seyoum Getu/DW

የታጋች ተማሪ ቤተሰቦች ጭንቀት


ባለፈው ሳምንት እረቡ ጠዋት ከአማራ ክልል ተነስተው ወደ አዲስ አበባ ስጓዙ የነበሩ ቁጥራቸው ከ 100 በላይ ይሆናል የተባሉ ተማሪዎች ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ አካባቢ በታጣቂዎች ከታገቱ በኋላ የተማሪዎቹ ቤሰተቦች በጭንቀት ላይ ወድቀዋል፡፡ አብዛኛዎቹየደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ናቸው የተባሉ ከአማራ ክልል ተነስተው ወደ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ በአውቶብሶች ሲጓዙ የነበሩ ከአንድ መቶ በላይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታግተው ከተወሰዱ በኋላ በአጋቾች እጅግ ከፍተኛ ገንዝብ መጠየቃቸውንም የታጋቾቹ ወላጆች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

ከአዲስ አበባ በስተ ሰሜን ወደ አማራ ክልል በሚወስደው አውራ ጎዳና 155 ኪሎ ሜትር ግድም ርቃ በምትገኘው ገርባ ጉራጫ አከባቢ ከተፈጸመው እገታ የተወሰኑ ተማሪዎች ሲያመልጡ ሌሎች ደግሞ ታግተው መወሰዳቸው ተሰምቷል። አብዛኛው ተማሪዎቹ መነሻቸውን ከአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ እና ከባሕር ዳር ያደረጉ መሆኑም ተነግሯል፡፡ ተማሪዎቹ ሲጓዙባቸው ከነበረው “ታታ” ከሚባሉ ሦስት የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ረቡዕ ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ካደሩበጽ ደጀን ከተማ ተነስተው ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት አከባቢ በታጣቂዎች መታገታቸው ነው የተነገረው።


የታጋቾች ዱካ መጥፋት
ሁለቱ አውቶብሶች ከደባርቅ ዩኒቨርስቲ፤ አንዱ አውቶብስ ደግሞ ከባሕር ዳር ከተማ (መናኸሪያ) ተነስተው ደጀን አድረው ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያሉ በጎሃ ጽዮን እና በቱሉ ሚልኪ መካከል እገታው ስለመፈጸሙም ተነግሯል፡፡ 
አንድ ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ወደ አዲስ አበባ እየመጣች ባለች ተማሪ እህታቸው መታገቷን እሮብ ጠዋት ሶስት ሰዓት ተኩል ግድም መስማታቸውን፤ ከእገታው ሁለት ቀናት በኋላ ዓርብ እለት ደግሞ በአጋቾች ገንዘብ መጠየቃቸውን ገልጸው አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ ተጎጂ ቤተሰብ፤ ታጋቾች እስከዛሬ ድረስ ከቦታ ቦታ ስጓዙ ከፍተኛ መሰቃየት ላይ መሆናቸውን መስማታቸውን አስረድተዋል። “ከተያዙበት እለት ጀምሮ እስከ ዛሬ ስጓዙ ነበር” ያሉት የታጋች ቤተሰብ ዛሬ ማለዳውን ተደውሎላቸው ህንኑን ማረጋገጣቸውንም ገልጸውልናል፡፡


በአጋቾች የሚቀርቡ የክፍያ ጥያቄዎች
ታጋቾቹ እሮብ ጠዋት ካደሩበት ደጀን ከተማ ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በሶስት አውቶብሶች እየተጓዙ ሳለ ገርባ ጉራቻ ሳይደርሱ በዚው አከባቢ መታገታቸውን የገለጹት አስተያየት ሰጪያችን፤ “እየሰማኋት በእለቱ እሮብ ቀን ታግተናል ወደ ጫካ እየተወሰድን ነው፤ ልንመለስም ላንመለስም እንችላለን ብላ ሄሎ እያልኳት ስልኳ ተዘጋ” ብለዋል፡፡ ዓርብ ቀንም አጋቾች በራሳቸው ስልክ አስደውለውአት ግማሽ ሚሊየን ብር መጠየቀዋን ከታጋቿ መስማታቸውን የገለጹት ቤተሰብ የተጠየቀው ገንዘብ በሶስት ቀን ውስጥ እንዲቀርብ መጠየቃቸውንም ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ 
ሌላው በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ስትማር የነበረችው የእህታቸውን መታገት ከአጋቾች የስልክ ጥሪ መስማታቸውን ገልጸው አስተያየታቸውን የሰጡን የሃዋሳ ከተማ ነዋሪ በአጋቾች ከባድ ያሉት ገንዝብ የክፈሉን ጥያቄ ቀርቧል ነው ያሉት፡፡ “ህጻኗ የሚታውቀው ነገር የላትም፡፡ ከትምህርቷ ነው እየተመለሰች ያለችው፡፡ እየጠየቁን ያለው ገንዘብ በአቅማችን የማይሞከር በመሆኑ ፈጣሪን እየተማጸን ነው ያለነው” ያሉት አስተያየት ሰጪው አጋቾች ደውለው 700 ሺኅ ብር ብተይቋቸውም ይህን ለመክፈል አቅም እንደሌላቸው አስረድተዋል፡፡


አስከፊዉ የቤተሰብ ጭንቀት


ያሉበትን ሁኔታ እጅግ “አሰቃቂ” በማለት የሚገልጹት የታጋች ተማሪዎቹ ቤተሰቦች በከፍተኛ ጭንቀት መዋጣቸውንም አስረድተዋል፡፡ “ከፍተኛ ኀዘን ውስጥ ነው ያለነው” የሚሉት ቤተሰAmharaየታገቱበት የሚያደርጉት ነግር አጥተው ግራ መጋባታቸውን አስረድተዋልም፡፡ ዶቼ ቬለ ተፈጽሟል ስለተባለው እገታም ሆነ በመንግስት ስለሚደረገው የማስለቀቅ ጥረት ለመጠየቅ በኦሮሚያ ክልል ለሰሜን ሸዋ ዞን ጸጥታ አስተዳደር ኃላፊ አቶ ሰለሞን አበባ የእጅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ በመደወል ጉዳዩን ብያስረዳቸውም ከ20 ደቂቃ በኋላ እንደሚደውሉ ገለጸው ከዚያን በተደጋጋሚ ብንደውልላቸውም ምላሽ አልሰጡንም፡፡ 
እገታው የተፈጸመበት አከባቢው መሰል ዜናዎች ስሰሙበት የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ከዚህ በፊትም በተለያዩ ጊዜያት እገታዎች ተፈጽመው ሰዎችን ለመልቀቅ ገንዘብ መጠየቁ ተደጋግሞ ስዘገብ ይታወሳል። በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ገንዘብ ለሚጠየቅባቸው እገታዎች መንግሥት “ሸኔ” የሚለው እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ቡድንን ተጠያቂ ያደርጋል። በታጣቂዎቹ በኩል ግን ይህ ስስተባበል እንጂ ስረጋገጥ እምብዛም አይስተዋልም፡፡

ሥዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ 

ፀሃይ ጫኔ