የታዳሽ ኃይል ማሽን ፈጣሪ እና ተሸላሚዎች | ባህል | DW | 20.12.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የታዳሽ ኃይል ማሽን ፈጣሪ እና ተሸላሚዎች

ሶስት ወጣቶች ናቸው። ማገዶን ከ50 ከመቶ በላይ ሊቆጥብ የሚያስችል ምድጃ እና የከሰል ማሽን በመሥራት ራሳቸውን አደራጅተው ሥራ የጀመሩ። እነዚህ ወጣቶችም በቅርቡ በታዳሽ ኃይል መስክ ለተሰማሩ ድርጅቶች እውቅና ከሚሰጠው የ(ኤስ ኢ ኢ ዲ ኢኒሽዮቲቭ) የ 2013ቱ ተሸላሚ ሆነዋል።

ወጣት ተራማጅ ተረፈ እሸቴ ፤ ይህንኑ የታዳሽ ኃይል ማሽን ከፈጠሩ እና ገበያ ላይ ካዋሉት ወጣቶች አንዱ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በጋራ ተደራጅተው በከፈቱት ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅት ውስጥ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ያገለግላል። ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት ተራማጅ እና ባልደረቦቹ የሠሩት ማሽን ጭስ አልባ ከሰል ነው የሚያመርተው። ወጣቱ ጭስ አልባነቱ የሚጀምረው ከከሰል መሥሪያው ማሽን ከሰሉ ከተሠራበት ተረፈ ምርቶች ማለትም ከግብዓቱ ነው ይላል። ይህን አብራርቶልናል።

ወጣቶቹ የፈጠሩት ከሰል በገበያ ላይ ውሏል። በህብረተሰቡም ዘንድ እጅግ ተፈላጊነት እንዳለው ተራማጅ ገልፆልናል። ፤ ይህም ወጣቱ እንደሚለው ከገንዘብ አኳያ ተመጣጣኝ ዋጋ ማለትም 1 ኪሎ ግራም በ4 ብር ስለሚሸጥ ነው።

ሁለቱ ባልደረቦቹ እና ተራማጅ አሁንም አብረው ነው የሚሰሩት። ከጥቃቅንና እና አነስተኛ ተነስተን አሁን ወደ መካከለኛ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅት ተሸጋግረናል ይላል፤ ሥራ አስኪያጁ፤ በጠቅላላው ቋሚ እና ጊዜያዊ ከ25-30 የሚደርሱ ሰራተኞች አሏቸው።

ወጣቶቹ ያላቸው ፈጠራ እና የምርት ውጤት በየዓመቱ በሚዘጋጀውየ የ(ኤስ ኢ ኢ ዲ ኢኒሽዮቲቭ) የ 2013ቱ ተሸላሚ እንዲሁኑ አብቅቷቸዋል። መቀመጫውን ደቡብ አፍሪቃ ያደረገው እና በታዳሽ ኃይል መስክ ለተሰማሩ ድርጅቶች ሽልማት የሚሰጠው ይህው ተቋም በተለያዩ ዘርፍ የተሰማሩ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶችን ያሳተፈ ውድድር ነበር ያካሄደው። ውድድሩ በጣም ፈታኝ ነበር ይላል ተራማጅ።

ወጣቱ ሌሎች የፈጠራ ሥራ ያላቸው ወጣቶች ሥራቸውን ለማን እና የት ማስተዋወቅ እንደሚችሉ ከራሱ ልምድ ጨምሮ ገልፆልናል። ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic