የታክሲ ዉስጥ ፅሁፎች | ኢትዮጵያ | DW | 23.03.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የታክሲ ዉስጥ ፅሁፎች

ሥነ-ልቡናዊ፥ ማሕበራዊ፥ ፖለቲካዊ፥ ሐይማኖታዊ እና ሌላም።ፅሁፉ ታክሲና ብጤዎቹን ሙጥኝ ማለቱ ግን፥ የድሬዳዋዉ ወኪላችን ዩሐንስ ገብረ-እግዚ አብሔር እንደሚያወጋን፥ የባሕል፥የእምነት፥የፖለቲካ ጫና በአደባባይ የመናገር መብትን ማገዳቸዉን ጠቋሚ ነዉ።

Autor/Copyright: Yohannes Gebreegziabher, Deutsche Welle Titel: Polizisten in Dire Dawa/Äthiopien Thema: Die Polizei - (nicht immer) Dein Freund und Helfer in Äthiopien Schlagwörter: Äthiopien, Polizei, Sicherheitskräfte Eingestellt 02/2011

ድሬዳዋ-ታክሲና ትራፊኩ

ላጭር ጊዜ ወደ አንድ አግጣጫ ከመጓዝ ባለፍ-ምንም የማይታዋወቁ መንገደኞች ባንድ አሳፍሮ ፊት-ለፊት አስቀምጦ የግድ ያሕል ለንግግር፥ ለወሬ፥ ለለከፋ፥ አንዳዴም ለተረብ፥ ጠብ በመጋበዙ ከመጓጓዣ-ታክሲነቱ ይልቅ አነጋጋሪነቱ አመዝኖ ዉይይት መጠሪያዉ ሆኖ ቀርቷል።ድሮ ጋሪ ፈረስ ላይ የደረሰዉ በሱም ደርሶ ከትላልቅ ከተሞች እያረቀ፥ ከገበያም እየወጣ ዘመኑ ያለፈበት ዉይይትን የተኩት ዘመነኛ ታክሲዮች እንደ ዉይይቱ በቃል-አላወያይ ብለዉ ነዉ መሰል በፅሑፍ ይዥጎረጎሩ ይዘዋል።ፅሁፉ ባብዛኛዉ አጫጭር ግን ቅይጥ ነዉ፥መልዕክቱም ብዙ።ሥነ-ልቡናዊ፥ ማሕበራዊ፥ ፖለቲካዊ፥ ሐይማኖታዊ እና ሌላም።ፅሁፉ ታኪሲና ብጤዎቹን ሙጥኝ ማለቱ ግን፥ የድሬዳዋዉ ወኪላችን ዩሐንስ ገብረ-እግዚ አብሔር እንደሚያወጋን፥ የባሕል፥የእምነት፥የፖለቲካ ጫና በአደባባይ የመናገር መብት-ድፍረትን ማገዳቸዉን ጠቋሚ ነዉ።

ዩሐንስ ገብረ-እግዚ አብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic