የታንዛኒያ ምርጫ እና ዉዝግብ | አፍሪቃ | DW | 28.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የታንዛኒያ ምርጫ እና ዉዝግብ

ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ እሁድ ዕለት ታንዛኒያ ዉስጥ የተካሄደዉ አጠቃላይ፤ ፕሬዝደንታዊ እና የአካባቢ ምርጫ ከወትሮ በተለየ መልኩ በምሥራቅ አፍሪቃ የተረጋጋች መሆኗ በሚነገርላት ሀገር ዉጥረት ያነገሰ መስሏል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:10
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:10 ደቂቃ

የታንዛኒያ ምርጫ እና ዉዝግብ

ለፕሬዝደንትነት ከተፎካከሩት መካከል የገዢዉ ቻማ ቻ ማፒንዱዚ፤ በምህጻሩ CCM እጩ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ቢጠቆምም፤ የተቃዋሚዉ ወገን ተፎካካሪ ድምጽ እንደገና መቆጠር እንዳለበት እያሳሰቡ ነዉ። ራስገዟ ደሴት ዛንዚባር ደግሞ የተቃዋሚ ፓርቲዉ እጩ አሸንፈዋል ብሎ ፓርቲዉ ቢገልፅም፤ የታንዛኒያ የምርጫ ኮሚሽን የተባለዉን ዉጤት ሰርዟል። ከሁለቱም ወገን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስለድምጽ ቆጠራዉ መጭበርበር ሲናገሩ፤ ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች አንዳንድ ችግሮች ታይተዋል ከማለት ዉጭ የእሁድ ዕለቱን የምርጫ ሂደት አወድሰዋል። ስለታንዛኒያ የምርጫ እና ዉዝግብ ናይሮቢ የሚገኘዉን ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማን በስልክ ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ አነጋግሬዋለሁ።

ፋሲል ግርማ/ ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic