የታቸር ቀብር | ዓለም | DW | 17.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የታቸር ቀብር

ብሪታንያ ዉስጥ ከቀድሞዋ የሐገሪቱ ልዕት ዳያና የቀብር ሥነ-ሥርዓት ወዲሕ በርካታ ሕዝብ ለሥንብት ሲወጣ የዛሬዉ የመጀሪያዉ ነዉ።ይሁንና ታቸርን የሚቃወሙ ሰዎችም አስከሬኑ ለሥንብት በተቀመጥበት አካባቢ ተሰልፈዉ ሟቿን ፖለቲከኛ ሲያወግዙ ነበር።ባለፈዉ ሳምንት ያረፉት የቀድሞዋ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ማርጋሬት ታቸር ዛሬ ተቀበሩ። በሥንብቱ ሥነ-ሥርዓት ላይ የብሪታንያዋን ንግሥት ጨምሮ የአንድ መቶ ሰባ ሐገራት መሪዎች፥ ሚንስትሮች፥ ባለሥልጣናትና በብዙ ሺሕ የሚቆጠር የብሪታንያ ሕዝብ ተገኝቷል።ብሪታንያ ዉስጥ ከቀድሞዋ የሐገሪቱ ልዕት ዳያና የቀብር ሥነ-ሥርዓት ወዲሕ በርካታ ሕዝብ ለሥንብት ሲወጣ የዛሬዉ የመጀሪያዉ ነዉ።ይሁንና ታቸርን የሚቃወሙ ሰዎችም አስከሬኑ ለሥንብት በተቀመጥበት አካባቢ ተሰልፈዉ ሟቿን ፖለቲከኛ ሲያወግዙ ነበር።የሥንብትና የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ እንዳይታጎል የብሪታን ፀጥታ አስከባሪዎች የለደን ከተማ በጥብቅ ሲቆጣጠሩ ነዉ የዋሉት።ታቸር በኑዛዛቸዉ መሠረት አስከሬናቸዉ ተቃጥሎ አመዱ ነዉ-የሚቀበረዉ።የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕን በሥልክ አነጋግሬዋለሁ።

ድልነሳ ጌታነህ

ነጋሽ መሐመድ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic