የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ | ኢትዮጵያ | DW | 15.08.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ

ኢትዮጵያ ውስጥ የታሰሩት የሙስሊሙ ማህረሰብ ተጠሪዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ተጠየቀ። መቀመጫውን አሜሪካን ያደረገው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ሂዩመን ራያትስ ዋች ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት አዲስ አበባ ውስጥ በሰላማዊ

default

ኢትዮጵያ ውስጥ የታሰሩት የሙስሊሙ ማህረሰብ ተጠሪዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ተጠየቀ። መቀመጫውን አሜሪካን ያደረገው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ሂዩመን ራያትስ ዋች ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት አዲስ አበባ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ባካሄዱ ሙስሊሞች ላይ በወሰደው እርምጃ ያሰራቸውን 17 ሃላፊነት የተሰጣቸውን የሙስሊም ማህበረሰብ ተወካዮች በአስቸኳይ እንዲለቅ ጠይቋል። እስረኞቹ በአግባቡ አለመያዛቸውን፤ የታሰሩትም ክስ ሳይመሰረትባቸው መሆኑንና ከጠበቃ ጋር እንዲነጋገሩ አለመደረጉንም ሂዩመን ራይትስ ዋች አስታውቋል። አንዳንዶቹም ዘመዶቻቸው እንዲያዩዋቸው አለመፈቀዱን ገልጿል። ሰዎቹ ቁም ስቅል በማሳየት በሚታወቅ እስር ቤት ተይዘው ጠበቃ ማግኘት ባለመቻላቸው ስጋቱን ከፍ እንደሚያደርገው አመልክቷል። ድርጅቱ፣ ፖሊስን ተቃዋሚዎችን በህገ ወጥ መንገድ በማዋከብ፤

ጥቃት በማድረስና በዘፈቀደ በማሰር ከሷል ። የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ በረከት ስምኦን ክሱን በማስተባበል የተፈፀመው እሥራት ህጋዊ መሆኑን አስታውቀዋል ። በድርጅቱ የአፍሪቃ ጉዳዮች ተመራማሪ ቤን ሮውለንስ የኢትዮጵያ መንግሥት የሙስሊሙን ማህበረሰብ ስሞታዎች በኃይል ሳይሆን በውይይት መፍታት እንደሚገባው እና የፀጥታ ኃይሎችም ህጉን ማክበር እንጂ መጣስ እንደሌለባቸው አሳስበዋል። ይሁንና አቶ በረከት ድርጅቱን ጣልቃ በመግባት ከሰው፣ ሀገሪቱ በማይታየው የሂዩመን ራይትስ ዋች እጅ ሳይሆን በህገ መንግሥት የምትመራ ናት ማለታቸውን የፈረንሳይ ዜና አግልግሎት ኤ ኤፍ ፒ ዘግቧል።

ሂሩት መለሠ

ተክሌ የኋላ

 • ቀን 15.08.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15qMC
 • ቀን 15.08.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15qMC