የታሰረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሆስፒታል ተወሰደ  | ኢትዮጵያ | DW | 30.03.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የታሰረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሆስፒታል ተወሰደ 

ባለፈው እሁድ በተመስገን ደሳለኝ መኖሪያ ቤት ከእስር ለተፈቱ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች ከተዘጋጀ ስነ ስርዓት ላይ ተይዘው የታሰሩት 11 ሰዎች የሚገኙበት ቦታ ለጤናቸው አስጊ መሆኑን የተመስገን ወንድም ለዶቼቬለ ገልጸዋል። እነዚሁ እስረኞች  ቀድሞ ተይዘውበት ወደ ነበረው ብዙ ሰዎች ወደሚገኙበት ጠባብ ክፍል ተዛውረዋል። 

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:24

እነ እስክንድር ወደ ጠባብ ክፍል ተዛውረዋል።

ባለፈው እሁድ ኮማንድ ፖስት ካሰራቸው ጋዜጠኞች ፖለቲከኞች እና ብሎገሮች አንዱ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታሞ ዛሬ ዘውዲቱ ሆሲፒታል ለህክምና መወሰዱን ወንድሙ ተናገሩ። ወንድሙ እንዳሉት ተመስገን ወደ ሆስፒታል የተወሰደው የጀርባ እና የወገብ ህመሙ ስለጠናበት ነው። ባለፈው እሁድ በተመስገን ደሳለኝ መኖሪያ ቤት ከእስር ለተፈቱ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች ከተዘጋጀ ስነ ስርዓት ላይ ተይዘው የታሰሩት 11 ሰዎች የሚገኙበት ቦታ ለጤናቸው አስጊ መሆኑን የተመስገን ወንድም ለዶቼቬለ ገልጸዋል። እርሳቸው እንዳሉት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ የሚገኙባቸው እነዚሁ እስረኞች  ቀድሞ ተይዘውበት ወደ ነበረው ብዙ ሰዎች ወደሚገኙበት ጠባብ ክፍል ተዛውረዋል። 
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 
ኂሩት መለሰ 
ነጋሽ መሐመድ 

Audios and videos on the topic