የቲምቡክቱ ሥመ-ጥር ልሒቅ፦አህመድ ባባ | ይዘት | DW | 14.08.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ይዘት

የቲምቡክቱ ሥመ-ጥር ልሒቅ፦አህመድ ባባ

በሰሜናዊ ማሊ የምትገኘው ቲምቡክቱ በአንድ ወቅት በነበራት ሐብት ሥመ-ጥር ነበረች። ከሰሐራ በርሐ ጠርዝ የምትገኘው ከተማ በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በእስላማዊ ትምህርት የከበረ ስም የተቸራት በንግድ ግንኙነትም የደመቀች ነበረች። ጨው፣ ወርቅ፣ የዝሆን ጥርስ እና ባሪያ የሚገበያዩ ነጋዴዎች ደጋግመው የሚገናኙባት መሆኗ ከተማዋን አድምቋታል። ለቲምቡክቱ ዝና የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ካበረከቱ መካከል አፍሪካዊው ታላቅ ምሁር አሕመድ ባባ አንዱ ናቸው።

ቪድዮውን ይመልከቱ። 01:24