የቱኒዚያ ከቀድሞው ስርዕት መላቀቅ | አፍሪቃ | DW | 12.11.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የቱኒዚያ ከቀድሞው ስርዕት መላቀቅ

ኢብቲህል አብደልላጢፍ በቀድሞው የቱኒዚያ አምባገነን ገዢ በዚን አል- አብዲን ቤን አሊ የቱኒዚያ ስርዓት ስር በደል የደረሰባቸውን ሰዎች ጉዳይ ይከታተላሉ። ወይዘሮዋ ቀደም ሲል በአንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ፣ አሁን ደግሞ በሀገሪቱ የሀቅ አጣሪ ኮሚሽን ውስጥ ያገለግላሉ።

«ውስጣችን ሞቶ ነበር፤ በዓብዮቱ ነፍስ አዘራን» ይላሉ ኢብቲህል አብደልላጢፍ። ወይዘrሮዋ የቱኒዚያ አምባገነን ስርዓት እአአ ጥር 14, 2011 ዓም ካከተመ በኋላ ወደ ከፍተኛ ተቋም ነው ያመሩት። አብደልላጢፍ ከ10 ዓመት በኋላ ዳግሞ ትምህርት ቤት ለመሄድ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በሐይማኖት ትምህርት ለመያዝ ተመዝግበው ነበር። የመማር፣ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ እና የፕረስ ነፃነት ለረዥም ዓመታት በአምባ ገነኑ ስርዕት ስር በቆየችው ቱኒዚያ ነፃ እየሆነ ነው። ለሲቪሉ ማህበረሰብ መብት የቆሙ ድርጅቶችም እየተቋቋሙ ነው።

የ 45 ዓመቷ አብደልላቲፍ ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ፤ ሲተረጎም« የቱኒዚያ ሴቶች»የሚል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት አቋቁመዋል። እስካሁን ከ 200 የሚበልጡ በፕሬዚዳንት ዚኔ አቢዲን ቤን አሊ የስልጣን ዘመን ከተቃዋሚው ፓርቲ የተሰለፉ እና በደል የደረሰባቸው ሴቶችን መዝግበዋል። የስራ ፍቃድ መከልከል፣ ወህኒ ቤት መግባት እና መደብደብ ብዙዎቹ የሚጋሩት ነው።«ቀጥሎ ምን እንደሚከሰት ማንም ያላወቀው ጊዜ፤ጥር 14፣ 2011 ዓ ም ፤ የደረቀ ዳቦ ስንበላ ያ ዳቦ እንዴት ይጣፍጥ ነበር። ምክንያቱም ነፃ ሆንን። ያ ነበር ጥሩው ነገር። አምባገነንነት፣ ጭቆና እና ጭፍጨፋ ጨርሶ ዳግም ሊመጣ አይገባም።»

Tunesien Wahlergebnisse

ምርጫ በቱኒዚያ

በማለት ነው አብደልላጢፍ ቱኒዚያ ውስጥ የነበረው ስርዓት ከአራት ዓመት በፊት ሲያበቃ የተሰማቸውን የገለፁት። ነገር ግን አምባ ገነኑ ስርዓት ካበቃበት ጊዜ አንስቶ ዕርቅ እስኪወርስ ረዥም ጊዜ ይፈጃል። የሽግግሩ የፍትህ ሥርዓት አሁን ድረስ የቱኒዚያ ፖለቲካ መነጋገሪያ ነው። በቅርቡ የተመረጠው ኮሚሽንም የቀየረው ነገር የለም። አብደልላጢፍ ስለ ፖለቲካ ግድ ካልሆነባቸው በቀር መናገሩን አይፈልጉም። ኮሚሽኑ ከህገ መንግሥቱ ጋር የተሳሰረ ነው። ስለዚህ ያንን የሚነካ ማንኛውም ነገር ሁሉም ፓርቲዎች ያፀደቁት ህገ መንግሥት ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል። ያ ከሆነ ደግሞ አደገኛ ነው።»

«የቱኒዚያ የፍትህ መዋቅር ከአመሰራረቱ አቅም የሌለው ነው» በማለት ሰዎች ሂስ ይሰነዘራል። ምክንያታቸውም ዘግይቶ የተመሰረተ እና በፖለቲካ የተሞላ ነው የሚል ነው። የዕውነት አጣሪው ኮሚሽን ገና ብዙ መሰናክሎችን መወጣት ይጠብቀዋል። ከተጎጂዎቹ መካከል ማን ካሳ ይሰጠው በሚለው ጥያቄም ያልተፈቱ ርዕሶች እንዳሉ አብደልላጢፍ ይናገራሉ። ኮሚሽኑ ሁሉን ያካተተ ነው። ከግራ የሴቶች መብት ተቆርቋሪ፣ እስከ ከውጭ ተመላሽ የመንግሥት ተቃዋሚዎች እና እንደ አብደልላጢፍ ፤ ወግ አጥባዊ ሙስሊሞችን ያቀፈ ነው። ይሁንና አሁን ሰላም ሰፍኗል ይላሉ ወይዘርዋ« ገና ብዙ የምንሰራው ነገር ይጠብቀናል። ስለዚህ ከስራችን ጋር ለማይገናኝ አለመግባባት ጊዜ አይኖረንም። »

ዋናው ነገር ይላሉ አብደልላቲፍ፤ ለተጎጆዎቹ የሚገባቸውን ክብር መልሶ መስጠት ነው። በአምባገነኑ ስርዓት ለተጎዱት ከገንዘቡ ካሳ ይልቅ የገጠማቸን በደል ከግምት ማስገባቱ ለነሱ ከምንም ነገር በላይ ክብደት ይኖረዋል።« በምንም ዓይነት በሞራል ያለውን አመኔታ ልናጣ አይገባም። ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ዜጎች በየዕለቱ የሚደርሰን ማሳሰቢያ ብዙዎች ትልቅ ተስፋ እንዳደረባቸው የሚያሳይ ነው። የዕውነት አጣሪ ኮሚሽኑ የክብር የዲሞክራሲ እና የዓብዮቱ ምልክት ነው። የተጎጂዎቹን መብት መልሶ የማስከበር ትልቅ ተስፋ ተጥሎበታል።»

የአምስት እህቶቻቸው ታላቅ የሆኑት አብደልላጢፍ የሀቅ አጣሪው ኮሚሽን ያላቸውን ኃላፊነት በውዴታ ነው የሚወጡት። በዛ ላይ ሰዎች በሙስሊም ሴቶች ላይ ያላቸውን አመለካከት ያስቀይራል ብለውም ያምናሉ። ወይዘሮዋ የ 3 ወንድ ልጆች እናት በሌላ በኩል ደግሞ ከስራ እና ትምህርት ጋር ጠባብ ጊዜ ነው ያላቸው ናቸው። ሆኖም ሰው የሚሰጣቸው ከበሬታ ፤ ትንሽም ቢሆን አላማቸው ከግብ መድረሱን አመላካች እንደሆነ ይናገራሉ።

ሳራ ሜርሽ / ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic