የቱርክ እና ሩሲያ አዲስ ግንኙነት | ዓለም | DW | 15.08.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የቱርክ እና ሩሲያ አዲስ ግንኙነት

ባለፈዉ ኅዳር ወር ቱርክ የሩሲያን የጦር ጀት በሶርያ ድንበሯ አቅራቢያ መትታ ከጣለች በኋላ ለወራት የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ቀዝቅዞ፤ በርቀት ወደ ቃላት ጦርነትም ገብተዉ ቆይተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:23

የታደሰዉ ግንኙነት

ሩሲያ ቱርክ ላይ የኤኮኖሚ ማዕቀብ መጣሏ፤ አንካራን ብቻ ሳይሆን ራሷም ላይ ችግር ማስከተሉ አልቀረም። ዉላ አድራ ቱርክ ባለፈዉ ሰኔ ጀቱን ለመጣሏ ይቅርታ ሩሲያን ጠይቃለች። በቅርቡ በፕሬዝደንት ኤርዶኻን መንግሥት ላይ መፈንቅለ ስልጣን ሲሞከር ደግሞ ከሌሎች ሃገራት አስቀድማ ሞስኮ፤ ለቱርክ መንግሥት ሃዘኔታዋን ገለጸች። ይህም ሁለቱ ሃገራት በመካከላቸዉ የተፈጠረዉን መቃቃር አስወግዶ ዳግም ወደ አዲስ ግንኙነት እንዲሻገሩ አድርጓቸዋል። የዕለቱ ማኅደረ ዜና ይህን ይዳስሳል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic