የቱርክ ሠራተኞች በጀርመን ሃምሳኛ ዓመት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 01.11.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የቱርክ ሠራተኞች በጀርመን ሃምሳኛ ዓመት

ከ 2ተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በጀርመን ግብዣ የልዩ ልዩ ሃገራት ዜጎች ከመንግስታቶቻቸው ጋር በተደረጉ ስምምነቶች ጀርመን ውስጥ ሲሰሩ ቆይተዋል ።

default

በዚህ መንገድ ወደ ጀርመን ለሥራ ከመጡት የውጭ ዜጎች ጣሊያኖች ፣ ስፓኞች ፣ ግሪኮች በኋላም ቱርኮች ይገኙበታል ። የቱርክ ሠራተኞች ምልመላ እስከ ቆመበት እ.ጎ.አ እስከ 1970 ዎቹ መጀመሪያ ድረስ በጀርመን ከሚሠሩት የውጭ ዜጎች ቱርኮች ከፍተኛውን ቁጥር ይይዙ ነበር ። ያኔ ቁጥራቸው ወደ 750 ሺህ ይጠጋ ነበር ። ዛሬም ቢሆን ጀርመን ውስጥ አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት የውጭ ዜጎች ቱርኮች ወይም መሠረታቸው የቱርክ የሆነ ናቸው ፤ ወደ 2.5 ሚሊዮን ይደርሳሉ ። ቱርኮች የዛሬ 50 ዓመት ወደ ጀርመን ለሥራ ሲመጡ ውላቸው እንዳበቃ ተመልሰው ወደ ሃገራቸው ይሄዳሉ ተብሎ ነበርና የሚታሰበው ጀርመን ጊዜያዊዎቹን ሠራተኞችና ነዋሪዎች የሚመለከት መርህ ማውጣት አላስፈለጋትም ነበር ። ይሁንና እ.ጎ.አ በ 1970 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ቁጥራቸው መጨመሩ ጉዳዩ እንዲተኮርበት ምክንያት ሆኗል ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic