የቱርክና የሶርያ ፍጥጫና ግጭት | ዓለም | DW | 04.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የቱርክና የሶርያ ፍጥጫና ግጭት

ትናንት ከሶርያ ምድር በተወነጨፈ ሞርታር አምስት ዜጎቿ የተገደሉባት ቱርክ የአፀፋ ጥቃት ሰነዘረች። በሁለቱ ተጎራባች ሀገሮች መካከል የተካረረዉ ፍጥጫ እንዲረግብ የአዉሮጳ ኅብረት ሲያሳስብ፤ የሰሜን አትላንቲ የጦር ቃል ኪዳን NATO በበኩሉ የሶርያን ርምጃ አዉግዟል።

ቱርክና ሶርያ ረጅም የድንበር አካባቢን ይጋራሉ። ወትሮዉኑ ከነበራቸዉ አለመጣጣም ጋ ተያይዞ የሶርያ አማፅያን በቱርክ ምድር መንቀሳቀስ ለደማስቆ ራስምታት ከሆነ ዉሎ አድሯል። ይህንንም የሶርያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሊድ አል ሙአለም በተመድጉባኤላይበግልፅአማፅያንንይደግፋሉያሏቸዉንሀገሮችጣልቃገብነትሲያወግዙቱርክንግንባርቀደምአድርገዉአመላክተዋል።ቱርክበበኩሏበደማስቆመንግስትላይየመንግስታቱድርጅትየፀጥታዉምክርቤትጠንከርያለርምጃእንዲወስድመወትወቷንቀጥላለች።የተበላሸዉንየሁለቱንሀገሮችግንኙነትደግሞሶርያ ወደቱርክ ግዛት የምትተኩሰዉ ሞርታር ይበልጥ እንዳሻከረዉ ነዉ የሚታየዉ። አሁን ቱርክ ከቀናት በፊት እንዳስጠነቀቀችዉ ከሶርያ ለሚሰነዘርባት የሞርታር ጥቃት አፀፋ መስጠት ጀምራለች። ትናንት ከሶርያ በድጋሚ የተወነጨፈዉ በደቡብ ምስራቅ ቱርክን ድንበር ተሻግሮ ቢያንስ ለአምስት ሲቪል የቱርክ ዜጎች ህልፈተ ህይወት ምክንያት ሆኗል። ለዚህም አንካራ የሰነዘረችዉ አሰፀፋ በርከት ያሉ የሶርያ ወደሮችን ሳይገድል አልቀረም። 

የጠቅላይ ሚኒስትር ራጂብ ኤርኻን መጽህፈት ቤት የወጣዉ መግለጫም ከሶርያ መንግስት የሚሰነዘረዉ ትንኮሳ ምላሽ ሳይሰጠዉ እንደማይታለፍ ግልፅ አድርጓል። የሀገሪቱ ምክትል ርዕሰ ብሄር ቡለንት አርኒክ ቱርክ እንደNATO አባልነቷ ሊደረግላት ይገባል ስላሉት ድጋፍ ሲናገሩ፤

«ይህ በቱርክ ግዛት ዉስጥ የደሰረና ሲቪሎች የተገደሉበት ጥቃት ነዉ። ዓለም ዓቀፉ ህግ ለዚህ ምላሽ እንደሚኖረዉ እርግጥ ነዉ። ቱርክ የNATO አባል ናት። በNATO ስምምነት ዉስጥ የሚገኙ አንቀፆች ከኃላፊነት ጋ የተገናኙ ናቸዉ። አንድ አባል ሀገር ጥቃት ሲሰነዘርበት መዘዝ ያስከትላል።»

ቀደም ብላም ቱርክ ለዚህ ጥቃት የተመድ የፀጥታዉ ምክር ቤት አስፈላጊ ያለችዉን ርምጃ እንዲወስድ በይፋ ጠይቃለች። የአንካራ ደማስቆን መተነኳኮስ ተከትሎም የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዲን NATO እና የመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታዉ ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ አካሂደዋል። NATO ሶርያ የምትሰነዝረዉን የኃይል ርምጃ ባስቸኳይ እንድታቆም ጠይቋል። በጋራ ባወጡት መግለጫም የNATO አምባሳደሮች እጅግ አሳሳቢ ያሉትን ጥቃት አባላቱ ሁሉ በጋራ አዉግዘዋል። የተመድ ዋና ፀሐፊ ባን ጊ ሙን የሶርያ መንግስት የጎረቤት ሀገራትን ሉዓላዊነት እንዲያከብር ጠይቀዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተንም ዋሽንግተን በድንበር ዘለሉ ጥቃት መቆጣቷን በማመልከት ከቱርክ አቻቸዉ ጋ እንደሚመክሩበት አስታዉቀዋል። የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተር ቬለም የፕሬዝደንት በሽር አልአሰድ መንግስት የጎረቤቶቹን ሉአላዊነት እንዲያከርብ አሳስበዋል፤

«የአሳድ አገዛዝ ባስቸኳይ የቱርክን ጨምሮ የሌሎች አጎራባች ሀገሮችን የድንበር ሉዓላዊነት እንዲያከብር አጥብቀን እንጠይቃለን። በተጨማሪም ይህንንም ግልጽ ማድረግ እፈልጋለሁ፤ እኛ የNATO አባል ከሆነችዉ አጋራችን ቱርክ ጎን እንቆማለን። ይህ ያለጥርጥር ይሆናል፤ ከዚህ ሌላ አስከፊዉ ሁኔታ እንዳይከተል ሰላም እንዲሰፍን እንጠይቃለን።»

የአዉሮጳ ኅብረት ሁለቱ ወገኖች አደብ እንዲገዙ ሲያሳስብ፤ ሩሲያ በበኩሏ ከሶርያ ወደቱርክ ድንበር የተሰነዘረዉ ጥቃት አጋጣሚ በመሆኑ አይደገምም የሚል ምላሽ ከደማስቆ ማግኘቷን ገልፃለች። ዘግይተዉ ከኢስታንቡል የወጡ ዘገባዎች እንዲሁ ሶርያ በተመድ በኩል ለጥቃቱ ይቅርታ መጠየቋን ያመለክታሉ።  በዛሬዉ ዕለት ከቀትር በኋላም የቱርክ ምክር ቤት መንግስት ሶርያ ላይ ወታደራዊ ርምጃ ለመዉስድ ያቀረበዉን ሃሳብ አፅድቋል።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic