የቱርኩ የ AKP ፓርቲ ድልና የኤርዶሀን ዕቅድ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 14.06.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የቱርኩ የ AKP ፓርቲ ድልና የኤርዶሀን ዕቅድ

እ.ጎ.አ ከ2002 ዓም አንስቶ ቱርክን የሚመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ታይፕ ኤርዶሀን በሃገሪቱ አብይ የሚባሉ በርካታ ለውጦችን ማስመዝገባቸው ደጋግመው ለመመረጣቸው ዋነኛው ምክንያት ነው ።

default

ኤርዶህንና ባለቤታቸው

ኤርዶጋን በተለያዩ ጊዜያት ባጋጥሙ የፋይናንስ ቀውሶች የሀገሪቱ ምጣኔ ሀብትና ፖለቲካ ተረግግቶ እንዲቀጥል ማስቻላቸው የህዝብ አመኔታን አትርፎላቸዋል ። በርሳቸው አመራር ዘመን ኢኮኖሚው በእጅጉ ተመንድጓል ። በአንድ ወቅት ወደ ፖለቲካው የገባውና በምርጫ ሥልጣን የያዙ መንግሥታትን እንደሻው ያስወግድ የነበረው ወታደሩ ፊቱን ከፖለቲካው እንዲያዞር ማድረጋቸውም ከኤርዶሀን ጉልህ ተግባራት ውስጥ ይደመራል ። እነዚህ ኤርዶሀን ያመጧቸው ለውጦች ለፓርቲያቸው ለ AKP የህዝብ ተወዳጅነትን አትርፈውለታል ።

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic