የቱርኩ የድንጋይ ከሰል ማውጫ አደጋ | ዓለም | DW | 14.05.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የቱርኩ የድንጋይ ከሰል ማውጫ አደጋ

ይሁንና በመኻሉ 450 ገደማ የሚሆኑትን ለማትረፍ ተችሏል። ማኒሳ በተባለው ክፍለ ሀገር ፤ ሶማ በተባለው ጣቢያ በሚገኘው የድንጋይ ከሰል ማውጫ ጉድጓድ አደጋ በደረሰበት ቅጽበት፤ ወደ 800 የሚጠጉ ሠራተኞ ች እንደነበሩ ተገልጿል።

በምዕራብ ቱርክ፤ በአንድ የድንጋይ ከሰል ማውጫ ጉድጓድ ውስጥ ተሠማርተው ከነበሩ ሠራተኞች መካከል በደረሰ አደጋ ሳቢያ ፤ 238 ሕይወታቸውን ማጣታቸው ተነገረ። 80 ያህል ቆስለዋል። የኃይል ምንጭ ጉዳይ ሚንስትር ታነር ይዲዝ እንዳሉት በመቶ የሚቆጠሩ የማዕድን ሠራተኞች በትኅተ ምድር መሿለኪው በር ተደርምሶ መውጫ አሳጥቶአቸ ው ነበር። ይሁንና በመኻሉ 450 ገደማ የሚሆኑትን ለማትረፍ ተችሏል። ማኒሳ በተባለው ክፍለ ሀገር ፤ ሶማ በተባለው ጣቢያ በሚገኘው የድንጋይ ከሰል ማውጫ ጉድጓድ አደጋ በደረሰበት ቅጽበት፤ ወደ 800 የሚጠጉ ሠራተኞ ች እንደነበሩ ተገልጿል። በኤልክትሪክ በተፈጠ ሳንክ ሳቢያ ቃጠሎ መነሳቱ ታውቋል። አደጋው፤ በቱርክ ሀገር በማዕድን ማውጫ ጉድጓዶች፣ የደሽንነት ዋስትና እስከምን ድረስ አስተማማኝነት እንዳለው ውቅታዊ የክርክር ርእስ ሆኗል። ይህ በአንዲህ እንዳለ የቱርክ መንግሥት 3 የኀዘን ቀናት ያወጀ ሲሆን፤

/ሚንስትር ሪጨፕ ጣይብ ኤርዶጋን፤ አደጋ የደረሰበትን ቦታ ሄደው ተመልክተዋል። ከኢስታንቡል በስተደቡብ ምዕራብ 250 ኪሎሜትር ራቅ ብሎ በሚገኘው ማዕድን ማውጫ ቦታ ስለደረሰው ዕልቂት የኃይል ምንጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ታነር ይዲዝ እንዲህ ነበረ ዛሬ ጧት ያገሪቱን ህዝብ ያረዱት።

«አሳዛኝ ሁኔታ ነው፤ የሞቱት ቁጥር ከ 200 በልጧል። እንደተገነዘብነው 201 ማዕድን አውጭ ሠራተኞች ሕይወታቸው አልፏል። 80 ቆስለዋል። ከቆሰሉት መካከል ሌሎች የማዕድን ሠራተኞች ያይደሉ ይገኙበታል። አንዳንዶቹ፤ በኋላ እዚያው ቦታ የደረሱ ነበሩ።»

በዛ ያሉ ሃገራት ከአነዚህም መካከል ፣ ጀርመን ፤ ግሪክና እሥራኤል ጭምርእርዳታ ለማቅረብ ዝግጁነታቸውን አስታውቀዋል። ፕሬዚዳንት ዮአኪም ጋውክና መራኂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ፤ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል። የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መሪ ፍራንሲስ ለሞቱት የነፍስ ይማር ፣ ለሟቾቹ ቤተሰብም መጽናናት ያገኙ ዘንድ ጸሎት አድርገዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በመዲናይቱ በአንካራ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አደባባይ ወጥተው በመንግሥት ላይ የተቃውሞ ሰልፍ በማሳየት፤ በፖሊሶችም ላይ ድንጋይ እስከመወርወር ደርሰው እንደነበረ ተገልጿል። ፖሊስ የሚያስለቅስ ጋዝና ውሃ በመርጨት ሰልፈኞቹን ለመበተን ሞክሯል።

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሀመድ