የተጠናከረ የጀርመን ነጻ ዴሞክራቶች ፓርቲ፡ ኤፍ ዴ ፔ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 28.09.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የተጠናከረ የጀርመን ነጻ ዴሞክራቶች ፓርቲ፡ ኤፍ ዴ ፔ

ትናንት በጀርመን የተካሄደው አጠቃላይ ምክር ቤታዊ ምርጫ ውጤት በትልቆቹ የክርስትያን ዴሞክራቶች ህብረት፡ ሴዴኡ እና በሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ፡ ኤስ ፔ ዴ መካከል ተቋቁሞ የነበረውን ትልቅ ጥምር መንግስት ፍጻሜ አስከትሎዋል።

default

የኤፍ ዴ ፔ ሊቀመንበር ጊዶ ቬስተርቬለ እና መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል

በክርስትያን ዴሞክራቶች ህብረትና በነጻ ዴሞክራቶቹ ፓርቲ መካከል ለሚመሰረት ጥምር መንግስት መንገድ አመቻችቶዋል።

Deutschland Bundestagswahlen 2009 CDU Feier

የመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ደጋፊዎች

በክርስትያን ዴሞክራቶች ህብረትና በነጻ ዴሞክራቶቹ ፓርቲ መካከል ለሚመሰረት ጥምር መንግስት መንገድ አመቻችቶዋል።

የክርስትያን ዴሞክራቶች ህብረትና የነጻ ዴሞክራቶቹ ፓርቲ በትናንቱ ምርጫ ያስቀመጡትን ዓላማ ከግብ አድርሰዋል። የክርስትያን ዴሞክራቶች ህብረትና እህት ፓርቲው የክርስትያን ሶሻል ህብረት፡ ሴኤስኡ ባንድነት በምርጫው ያገኙት ውጤት (33.8%)ባለፈው ምርጫ ካገኙት አነስ ያለ ቢሆንም፡ በዚሁ ምርጫ ብዙ የመራጭ ድምጽ በማግኘት ከተጠናከረው የነጻ ዴሞክራቶቹ ፓርቲ(14.6%)ር ባንድነት በመሆን ጥምር መንግስት ለመመስረት ይችላሉ። የሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ ትልቅ ሽንፈት ደርሶባቸዋል።

የሴዲኡ ሊቀመንበርና መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የሁሉም ጀርመናውያን መራሂተ መንግስት የመሆን ዕቅድ እንዳላቸው ከምርጫው ውጤት መታወቅ በኋላ በሰጡት ቃለ ምልልስ አረጋግጠው፡ሁለቱ ወገኖች ዛሬ የመጀመሪያ ውይይት እንደሚያካሂዱ አስታውቀዋል።

ሶሻል ዴሞክራቶቹ ከአራት ዓመት በፊት በተካሄደው አጠቃላይ ምርጫ አግኝተውት ከነበረው የመራጭ ድምጽ በአስራ አንድ ከመቶ ዝቅ ያለ ድምጽ ሲያገኙ(22.9%) ፡ ከሀምሳ ስድስት ዓመት ወዲህ ይህ ዓይነቱ ሽንፈት ሲደርስባቸው ይህ የመጀመሪያው ነው።

በትናንቱ አጠቃላይ ምርጫ ከኤፍዴፔ ሌላ ብዙ የመራጭ ድምጽ በማግኘት የተጠናከሩት ሌሎቹ በምክር ቤት የሚወከሉት የግራ ፓርቲ(12,1%) እና የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ (10,7%) ናቸው።

አርያም ተክሌ