የተገኘዉ የአዉሮፕላን ስባሪ ከየት መጣ? | ሳይንስ እና ህብረተሰብ | DW | 05.08.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ህብረተሰብ

የተገኘዉ የአዉሮፕላን ስባሪ ከየት መጣ?


ከማሌዥያ ኳላላምፑር ወደ ቻይና ፔኪንግ 239 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ የመንገደኞች ማመላለሻ አዉሮፕላን ከጠፋ አንድ ዓመት ከመንፈቅ አስቆጠረ። ከማዳጋስካር 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ሪዩኒየን ደሴት የባህር ጠረፍ ላይ ከተገኘዉ የአዉሮፕላን ስባሪ ምናልባት የጠፋዉ የማሌዢያ አዉሮፕላን አካል ሳይሆን እንዳልቀረ እየተነገረ ነዉ። ምንም እንኳ እስካሁን ማረጋገጫ ባይሰጥም። የዉቅያኖስ ዉኃ ዝዉዉር አጥኚዎች እንደሚሉት ደግሞ የተገኘዉ የአዉሮፕላን ስባሪ ይወድቃል ተብሎ ከታሰበበት በ 17 ወራት ጊዜ ዉስጥ ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ መገኘቱ የሚታመን ነዉ ። በዕለቱ ዝግጅታችን የተሰወረዉን የማሌዥያ አዉሮፕላን MH370 ጉዳይ የባህር ዉኃ ንቅናቄ አጥኝዎች ትንታኔን እንቃኛለን።

Audios and videos on the topic