የተገን ጠያቂዎች መብትና ረቂቁ ደንብ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 25.09.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የተገን ጠያቂዎች መብትና ረቂቁ ደንብ

የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ላይ በአውሮፓ ተገን ጠያቂዎች በአግባቡ እንዲያዙ ያግዛል ያለውን ረቂቅ ደንብ አውጥቷል ። ደንቡ በእስካሁኑ የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የተገን ጠያቂዎች አያያዝ ላይ የተወሰኑ ማሻሻያዎች አድርጓል ።

የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የሲቪል ነፃነት ኮሚቴ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ባካሄደው ድምፅ አሰጣጥ አሁን በሚሰራበት የአውሮፓ ህብረት የስደተኞች አቀባበልና አያያዝ ላይ ማሻሻያዎችን ያደረገ ረቂቅ ደንብ አጽድቋል ። ረቂቁ ተገን ጠያቂዎች የሚያዙበትን ምክንያት የሚገድብ ፣ የሚያዙባቸው ሁኔታዎች እንዲሻሻሉ የሚጠይቅና ከለላ እንዲሰጣቸው ባመለከቱበት አገር ሥራ የሚጀምሩበትን የጊዜ ገደብ ከቀድሞው የሚያሳጥር ነው ። ከዚሁ ጋርም ስለ ሚያስፈልጓቸው የጤና ምርመራዎች አስቀድሞ ጥናትና ክትትል ማድረግንም ያካትታል ። ከረቂቅ ደንቡ የተወሰነው ክፍል ሲወደስ አንዳንዱ ክፍል ደግሞ ተተችቷል ። ። እጎአ የ 2003 ቱ የአውሮፓ ህብረት የተገን አሰጣጥ ደንብ ላይ ማሻሻያ ያደረገው አዲሱ ረቂቅ  የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤትን ስምምነት አግኝቷል ። የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ እንዳስታወቀው ከህብረቱ ምክር ቤት ጋር በረቂቅ ደንቡ ላይ ስምምነት ላይ የተደረሰው ከ4 አመታት ድርድር በኋላ ነው ። በረቂቁ ውስጥ ከተካተቱት ማሻሻያዎች አንዱ ተገን ጠያቂዎች የሚያዙበትን አግባብ የሚመለከተው ክፍል ይገኝበታል ። ረቂቁ የተገን ጠያቂዎችን አቀባበል ና አያያዝ ደረጃዎች ምን መሆን እንደሚገባቸውም በዘረዘረበት ደንብ ተገን ጠያቂዎች  በሚከተሉት  6 ምክንያቶች ብቻ መያዝ እንዳለባቸው አስቀምጧል ። በዚሁ መሰረት አንድ ተገን ጠያቂ የሚያዘው

አንደኛ የተገን ጠያቂውን ማንነት ለማጣራት ፣ ሁለተኛ ዓለም አቀፍ ከለላ እንዲሰጠው ወይም እንዲሰጣት ያስገባው ያስገባችው ማመልከቻ የያዛቸውን ጉዳዮች ለማጣራት ፣ ሶስተኛ

ወደ አንድ አባል ሃገር ግዛት የመግባት መብት ላይ ውሳኔ ለመስጠት

አራተኛ ብሄራዊ ፀጥታንና ስርዓትን ለማስጠበቅ ፣ አምስተኛ ተገን ጠያቂው ዓለም አቀፍ ጥበቃ እንዲደረግለት ያመለከተው ወደ ሃገሩ እንዳይመለስ ለማዘግየት አሰቦ ነው ተብሎ ከታመነበት ወደ ሃገሩ እንዲመለስ ዝግጅት ለማድረግ

6 ተኛ በደብሊኑ ስምምነት መሠረት ተገን ጠያቂውን ወደ ሌላ የህብረቱ አባል አገር ማስተላለፍ ሲያስፈልግ ነው ። ይሁንና ለተገን ጠያቂዎች መብት የቆሙ አንዳንድ ድርጅቶች ማሻሻያው አሁንም ግልፅ ባለመሆኑ አሳስቧቸዋል ። ማራይ ፔልሰር መንግስታዊ ባልሆነው ለተገን ጠያቂዎች መብት በሚታገለው ፕሮአዙል በተባለው ድርጅት የህግ ባለሞያ ናቸው ። በርሳቸው አስተያየት በረቂቁ ደንብ የተቀመጡት ተገን ጠያቂዎች የሚታሰሩባቸው ምክንያቶች ግልፅ አይደሉም ። ፔልሰር እንደሚሉት በማሻሻያው የተዘረዘሩት ምክንያቶች በአንዳንድ ሃገራት ተገን ጠያቂዎች በዘፈቀደ መታሰራቸውን ህጋዊ የሚያደርግ ነው ።

እንዳለባቸው አስቀምጧል ። በዚሁ መሰረት አንድ ተገን ጠያቂ የሚያዘው

« ሰዎች እንዲታሰሩ በምክንያትነት የተጠቀሱት 6 ጉዳዮች ለሚያዙት ሰዎች ሁሉ ምክንያት አድርጎ ለማቅረብ በጣም አስቸጋሪ መሆኑን አይተናል ። ምክንያቱም ይህ የሚታሰሩበት ምክንያት በብዙ ሃገሮች ለምሳሌ እንደ ሃንጋሪና ግሪክ በመሳሰሉት ሃገራት ህጋዊ አፈፃፀሙ አይከበርም ወይም በነዚህ ሃገሮች ሰዎችን በዘፈቀደ ለማሰር መሣሪያ ነው የሆነው ። »

በአሁኑ ሰአት እጅግ ብዙ ስደተኞችን በማስተናገድ ግንባር ቀደሙን ስፍራ ከሚይዙት የአውሮፓ ህብረት አባል አገሮች አንዷ ግሪክ ናት ። በግሪክ የስደተኞች አያያዝ እጅግ አስከፊ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት በአካል ተገኝተው ያረጋገጡት ጉዳይ ነው ። በማልታም እንዲሁ ችግሩ የከፋ ነው ። ረቂቅ ደንቡ በነዚህ ሃገራት ለውጥ ማምጣቱ ቀርቶ ተገን ጠያቂዎች እንዲገላቱ ያደርጋል ባይ ነው ፕሮአዙል ። እ.ጎ.አ የ 2003 አመተ ምህረቱ የአውሮፓ ህብረቱ ደንብ ተገን ጠያቂዎች የሚታሰሩባቸውን ምክንያቶች በግልፅ አላስቀመጠም ። በዚህ የተነሳም ተገን ጠያቂዎች የሚያዙበት ሁኔታ አተረጓጎም ለአባል ሃገራት ክፍት የተተወ ነበር ። በረቂቅ የተገን ጠያቂዎችን አያያዝ በተመለከተም በአጠቃላይ እንደ መመሪያ የተቀመጠው በተለዩ የማቆያ ስፍራዎች መያዝ እንዳለባቸው ነው ። ሆኖም አንድ የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገር አመልካቹን በዚህን መሰል ማዕከል ማቆየት ካልቻለ ና ግለሰቡን ወህኒ ቤት ለማስገባት ከተገደደ አመልካችዋ ወይም አመልካቹ ከሌሎች እስረኞች በተለየ ስፍራ መያዝ እንዳለባቸው ቦታውም አየር ማግኝት የሚችሉበት ሊሆን እንደሚገባ በአዲሱ ረቂቅ ተመልክቷል ። ከዚሁ ጋርም አመልካቾች መብቶቻቸውንና ግዴታዎቻቸውን በሚረዱበትና ይረዳሉ ተብሎ በሚታሰብበት ቋንቋ ሊብራራላቸው እንደሚገባም በማሻሻያው ተጠቅሷል ።

ስምምምነት ላይ በተደረሰበት በአዲሱ ደንብ መሰረት ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች የሚታሰሩት እማራጭ ሲጠፋ መሆን እንደሚገባው ሃሳብ ይሰጣል ። በማሻሻያው እንደተጠቀሰው ሊታሰሩ የሚችሉት እጅግ በተለየ ምክንያት መሆን ነው ያለበት ።የሚያዙት ለአጭር ጊዜ መሆን ሲገባው በተቻለ ፍጥነት ተለቀው አመቺ ወደ ሆነ ስፍራም መወሰድ ይኖርባቸዋል ። እነዚህ ልጆች እስር ቤት ውስጥ መያዝ እንደሌለባቸው ከአዊቂዎች ተለይተው የሚያስፈልጓቸው ነገሮች ባሉበት ስፍራ መያዝ እንደሚገባቸው ነው በረቂቁ የሰፈረው ። ሆኖም እንደ ፕሮአዝዩልዋ ፔርሰል የተሻሻለው ደንብ አስገዳጅ ባለመሆኑ ያን በጥሩ ጎኑ የሚነሳ አይደለም

« የልጆችን አያያዝ በተመለከተ የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የኮሚሽኑን ስምምነት እንዲቀበሉ ሃሳብ ከመስጠት ውጭ ጠንካራ  ወይም አስገዳጅ ደንብ ስለሌለው ለአካለ መጠን ያልደረሱ ተገን ጠያቂዎችን ለመንከባከብ ምንም አይነት የተወሰደ ጥሩ እርምጃ አላየሁም ። » 

እንዳለባቸው አስቀምጧል ። በዚሁ መሰረት አንድ ተገን ጠያቂ የሚያዘው

ፌስቱስ ታናዊ ካካሜሩን ወደ ጀርመን የተሰደደ ተገን ጠያቂ ነው ። ከጀርመን መዲና በርሊን ወጣ ብሎ በሚገኝ የተገን ጠያቂዎች መጠለያ ውስጥ ነው የሚኖረው ። ለጥገኝነት ላስገባው ማመልከቻ የጀርመን ባለሥልጣናት የሚሰጡትን ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል ። የጀርመን መንግሥት ከለላ እንዲሰጠው ካመለከተ አንድ አመት ሆኖታል ። እስካሁን ግን የሥራ ፈቃድ የለውም ። ባለፈው ሳምንት የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ባወጣው አዲስ ረቂቅ ደንብ መሠረት ወደፊት ተገን ጠያቂዎች በአንድ የህብረቱ አባል ሃገር አለም አቀፍ  ከለላ እንዲሰጣቸው ካመለከቱ ከ 9 ወር በኋላ ሥራ እንዲጀምሩ ይፈቅዳላቸዋል ። አሁን በሚሰራበት ደንብ ግን ተገን ጠያቂዎች መሥራት የሚችሉት ከለላ እንዲሰጣቸው ካመለከቱ ከአንድ አመት በኋላ ነው ። በዚህ መሰረት ካሜሩናዊው ፌስቱስ ሥራ መያዝ ይፈቀድለታል ። ሆኖም እርሱ ለሚያመለክትበት ሥራ የአውሮፓ ህብረት ዜጋ ካልተገኘ ነው ሥራው ሊሰጠው የሚችለው ። ይህ በደንቡ ላይ የሰፈረው አሰራር ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው ግን በየሃገሩ ህግና ደንብ መሰረት በሚገኘው የሥራ ፈቃድ መሠረት መሆኑ የተቀመጠውን ደንብ በአባል ሃገራት በሙሉ ተግባራዊ መሆኑን አጠያያቂ ማድረጉ አልቀረም ። ያም ሆኖ ፕሮአዝዩል ይህ ትልቅ እርምጃ ነው ሲል አወድሶታል ። የጀርመን መንግሥትም ሌሎች ሃገራት ማሻሻያውን እንዲደግፉ ግፊቱን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል

« ጀርመን መንግሥታቱ ለስደተኞች ድጋፍ የመስጠቱን ኃላፊነት እንዲወስዱ ግፊት የማድረጉን መርህ ማጠናከር በሚለው አቋሟ መፅናት አለባት ። »

አዲሱ ረቂቅ ማሻሻያ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የነፃነት ኮሚቴ 45 አባላትን ድጋፍ ሲያገኝ 9 ተቃውመውታል ። በ 4 ደግሞ በድምፀ ተአቅቦ አልፈውታል ። ረቂቁ ህግ ሆኖ ከመውጣቱ በፊት አባል ሃገራት ስምምነት ላይ የተደረሰበትን ማሻሻያ ማፅደቅ ይኖርባቸዋል ። ከዚያም ስምምነቱ ወደ ፓርላማው ተመልሶ የጎርጎሮሳውያኑ 2012 አመተ ምህረት ከማብቃቱ በፊት ድምፅ ይሰጥበታል ተብሎ ይጠበቃል ። ማሻሻያው ከፀደቀ በኋላ የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ህጉን በብሄራዊ ህጋቸው ውስጥ ለማካተት የ 2 አመት ጊዜ ይሰጣቸዋል ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዮ ለገሰ

Audios and videos on the topic