የተካረረው የቱርክና የሶርያ ውዝግብ | ዓለም | DW | 11.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የተካረረው የቱርክና የሶርያ ውዝግብ

በድንበር ግጭት እና በሰበቡ በተከተለው የአምስት ሰዎች ሞት የተቀሰቀሰው የቱርክና የሶርያ ውዝግብ ከትናንት ጀምሮ ሌላ መልክ ይዞዋል። የቱርክ የጦር አይሮፕላኖች ትናንት አንድ ከሞስኮ ወደ ደማስቆ ይበር የነበረ የሶርያ የመንገደኞች ማመላለሻ አይሮፕላን አስገድደው አንካራ ላይ ካስወረዱ ወዲህ ከሁለቱም ወገኖች ጠንከር ያለ ክስ ይሰማል።


በሶርያ አይሮፕላን ውስት የጦር መሳሪያ ማግኘቱን የቱርክ መንግሥት ከሶዋል። በቱርክ ርምጃ ቅር የተሰኙት የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲንም በቅርቡ ወደ አንካራ ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት ከመሰረዛቸውም በላይ ከቱርክ ማብራሪያ ጠይቀዋል።

ይልማ ኃይለሚካኤል
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic