«የተከፈለው ዋጋ መና አልቀረም» የ ዞን 9 ጦማሪ አቤል ዋቤላ  | ወጣቶች | DW | 31.05.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ወጣቶች

«የተከፈለው ዋጋ መና አልቀረም» የ ዞን 9 ጦማሪ አቤል ዋቤላ 

አቤል ዋቤላ በኢትዮጵያ መንግሥት በሽብር ወንጀል ተከሶ ለ አንድ አመት ተኩል ያህል በእስር ማሳለፉ ይታወሳል። አቤል ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ሲገመግም የተሻለ ነገር እንዳለ ነገር ግን ብዙ እንደሚቀር ይናገራል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:09

«የተከፈለው ዋጋ መና አልቀረም» የ ዞን 9 ጦማሪ አቤል ዋቤላ 

አቤል ዋቤላ ከ ዞን 9 ጦማሪዎች አንዱ ነው። በኢትዮጵያ መንግሥት በሽብር ወንጀል ተከሶ ለ አንድ አመት ተኩል ያህል በእስር ማሳለፉ ይታወሳል። አቤል ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ሲገመግም የተሻለ ነገር እንዳለ ነገር ግን ብዙ እንደሚቀር ይናገራል። « የተከፈለው ዋጋ መና አልቀረም። ጥሩ የሚባሉ ጅምሮች አሉ። ግን የመናገር ነፃነት መብትን በሀገሪቱ ለማስከበር በጣም ገና ነን ብዬ አስባለሁ።» ይላል።  አቤል በአሁኑ ሰዓት ከጓደኞቹ ጋር አዲስ ዘይቤ የሚባል የኦላይን ሚዲያ አደራጅቶ በመስራት ላይ ይገኛል። ወጣቱ ዶይቸ ቬለ ካዘጋጀው የዘንድሮው የአለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን መድረክ ተካፋዮች አንዱ ነበር። በዚህም መድረክ እንደሱ ተመሳሳይ ሀሳቦችን የሚጋሩ ታዳሚዎች ገጥመውታል። አቤል በእስር መስዋትነት ያስከፈሉት «የህግ የበላይነት፣ ህገ መንግሥታዊነት ፣ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ይከበር የሚሉና ሌሎች ማህበረሰባዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በማንሳቱ ነው። ወጣቱ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በአለም ዙሪያ እንዲከበር በመሳተፉ  ትልቅ ደስታ እንደሚሰማውም ለDW ገልጿል። ከአቤል ዋቤላ ጋር የተደረገውን ሙሉውን ቃለ መጠይቅ በድምፅ መከታተል ይችላሉ። 


ልደት አበበ 

Audios and videos on the topic