የተባባሰዉ የአየር ብክለትና መዘዙ | ጤና እና አካባቢ | DW | 07.03.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

የተባባሰዉ የአየር ብክለትና መዘዙ

የዓለም የጤና ድርጅት ባለፈዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ግንቦት ወር ላይ ይፋ ያደረገዉ ቅኝት ዉጤት መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸዉ አብዛኛዉ ሃገራት ከተሞች የአየር ብክለት መጠኑ ከፍ እያለ መሄዱን አመላክቷል። የተበከለ አየር የታመቀባቸዉ ከተሞች ነዋሪዎችም ለተለያዩ የጤና እክሎች መጋለጣቸዉንም ገልጿል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:38

አየር በካዩ የመኪና ጭስ

የዓለም የጤና ድርጅት በ103 ሃገራት የሚገኙ 3000 ከተሞችን ያካተተ የአየር ብክለት ይዞታ ቅኝት ማካሄዱን የድርጅቱ ሰነዶች ያመለክታሉ። እንደጥናቱም እነዚህ ከተሞች ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸዉ፤ ከ100 ሺህ የሚበልጡ ነዋሪዎችን የሚያካትቱ ሲሆኑ፤ አየራቸዉ የዓለም የጤና ድርጅት ለጤና ተስማሚ የሚለዉን የጥራት ደረጃ አያሟላም።

መኖሪያቸዉን በዩናይትድ ስቴትስ ካሊፎርኒያ ግዛት ካደረጉ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠሩት ኢንጂነር ደርበዉ ሸንቁጥ  ከብዙ ዓመታት ቆይታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትዉልድ ሀገራቸዉ ሲመለሱ በከተሞች በተለይም በአዲስ አበባ ከፍተኛ የአየር ብክለት መኖሩን እንዳስተዋሉ ይናገራሉ።

እሳቸዉ እንደሚሉትም ተሽከርካሪዎች በአግባቡ አለመጠገን እና ክብካቤ አለማግኘታቸዉ ከባቢ አየሩን እንዲበክሉ ምክንያት ሆኗል። የሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ባለሙያ መሆናቸዉን የሚናገሩት ኢንጂኒየር ደርበዉ፤ ዋና ሙያቸዉ የአዉቶሞቢል ኢንጂኒየሪንግ እንደሆነ እና ለአሜሪካ መንግሥት ከመኪና የሚለቀቅ ጭስን የሚቆጣጠር መሥሪያ ቤት ሠራተኛ መሆናቸዉን ገልጸዋል። እናም ላለፉት 25 ዓመታት በዚህ ዘርፍ ሠርተዋል። በዚህ ዘርፍ እንደሚሠራ ባለሙያም አዲስ አበባ በሄዱበት ወቅት ያስተዋሉት ነገር አሳስቧቸዉ ለሚመለከታቸዉ የኢትዮጵያ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችም ጉዳዩን ቢያሳዉቁም ከብዙ ሙከራ በኋላ ራሳቸዉ ኃላፊነት ለመዉሰድ መወሰናቸዉንም ይገልጻሉ።  ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተመልሰዉም በዘርፉ ባለሙያዎች ከሆኑ ሌሎች ባልደረቦቻቸዉ ጋር በመምከር የበኩላቸዉን አስተዋጾኦ ለማድረክ ወሰኑ። ዝርዝር መረጃዉን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic